የኢራን-እስራኤል ፍጥጫ፦ የሰኔ 18 ጠዋት ወቅታዊ ዜናዎች

© telegram sputnik_ethiopia / ወደ ፎቶ ባንክ ይሂዱየኢራን-እስራኤል ፍጥጫ፦ የሰኔ 18 ጠዋት ወቅታዊ ዜናዎች
የኢራን-እስራኤል ፍጥጫ፦ የሰኔ 18 ጠዋት ወቅታዊ ዜናዎች - Sputnik አፍሪካ, 1920, 25.06.2025
ሰብስክራይብ

የኢራን-እስራኤል ፍጥጫ፦ የሰኔ 18 ጠዋት ወቅታዊ ዜናዎች

🟠 የኢራን ፓርላማ ሀገሪቷ ከዓለም አቀፉ የኒውክሌር ተቆጣጣሪ ኤጄንሲ ጋር የነበረውን ትብብር የሚያቋርጥ ረቂቅ ሕግ ያፀደቀ ሲሆን በዚህም የኤጀንሲው ሠራተኞች የኒውክሌር ተቋማትን ለመፈተሽ ሀገሪቱን መጎብኘት አይችሉም፡፡

🟠 ከሰኔ 6 ጀምሮ ኢራን ውስጥ 700 ሰዎች ለእስራኤል በመሰለል ተጠርጥረው ታስረዋል ሲል የሀገር ውስጥ መገናኛ ብዙኃን ዘግበዋል።

🟠 የኢራን ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አባስ አራግቺ ሰኞ ዕለት ከሩሲያ ፕሬዝዳንት ቭላድሚር ፑቲን ጋር ያደረጉት ውይይት ጥሩ እንደነበር ገልፀው ሞስኮ የአሜሪካ እና የእስራኤል ጥቃትን በተመለከተ ጥብቅ አቋም መያዟን አስታውቀዋል።

🟠 የአሜሪካ ጥቃት የኢራንን የኒውክሌር መርሃ ግብር ዋና ዋና ክፍሎች አላጠፋም፤ ነገር ግን እድገቱን ለወራት "ወደ ኋላ እንደጎተተው" አንዳንድ የአሜሪካ ሚዲያዎች የደህንነት መረጃዎችን ጠቅሰው ዘግበዋል።

🟠 በምላሹ የአሜሪካ ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ አሜሪካ በኢራን ላይ የወሰደችውን ጥቃት ለማጣጣል ሞክረዋል ሲሉ ሚዲያዎቹን ከሰዋቸዋል፡፡

🟠 የአሜሪካ ፕሬዝዳንት ልዩ መልዕክተኛ ስቲቭ ዊትኮፍ ዋሽንግተን ከኢራን ጋር ሁሉን አቀፍ የሰላም ስምምነት ላይ መድረስ እንደምትችል እምነታቸውን ገልጸዋል።

🟠 የምዕራባውያን መገናኛ ብዙኃን በኢራን ሰላማዊ የኒውክሌር ተቋማት ላይ የሚደረጉ ጥቃቶች በታሪክ የመጀመሪያው እንደሆኑ ባለመዘገባቸው ሙያዊ ወንጀል ሠርተዋል ሲሉ የሩሲያ ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ ማሪያ ዛካሮቫ ተናግረዋል።

በእንግሊዘኛ ያንብቡ

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X

አዳዲስ ዜናዎች
0