የኢራን-እስራኤል ግጭት የዛሬ ምሽት ቁልፍ ክስተቶች፦
19:52 24.06.2025 (የተሻሻለ: 20:04 24.06.2025)

© telegram sputnik_ethiopia
/ ሰብስክራይብ
የኢራን-እስራኤል ግጭት የዛሬ ምሽት ቁልፍ ክስተቶች፦
⏺ የእስራኤል ጦር ከተኩስ አቁሙ በኋላ ኢራን ሚሳኤል ተኩሳለች ብሏል። ኢራን አስተባብላለች።
⏺ ኢራናዊው የኒውክሌር ሳይንቲስት ሞሐመድ ረዛ ሰዲግ ከተኩስ አቁሙ በፊት በእስራኤል ጥቃት ተገድለዋል።
⏺ ትራምፕ ኢራን እና እስራኤል የተኩስ አቁም ስምምነቱን እንደጣሱና በሁለቱ ወገኖች ቅር እንደተሰኙ ገልፀዋል።
⏺ እስራኤል የተኩስ አቁም ስምምነቱን በመጣስ በሰሜን ኢራን ባዶ ቦታዎችን ደብድባለች።
⏺ ኢራናውያን የኒውክሌር ሳይንቲስቶች ቤተሰብና ልጆቻቸውን ጨምሮ በእስራኤል ጥቃቶች ተገድለዋል።
⏺ የኢራን ጤና ሚኒስቴር በእስራኤል ጥቃት 610 ሰዎች መሞታቸውንና 4 ሺህ 746 ሰዎች መቁሰላቸውን አስታውቋል።
⏺ ቴህራን ከእስራኤል ጋር የተደረገውን የተኩስ አቁም እንደምታከብር እና ለድርድር ዝግጁ መሆኗን አስታውቃለች።
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X