አሜሪካ ኢራንን መደብደቧ በአውሮፓ ህብረት እና በአሜሪካ መካከል ያለውን አለመግባባት ያሳያል ሲሉ የፈረንሳይ የአውሮፓ ፓርላማ አባል ተናገሩ

© telegram sputnik_ethiopia / ወደ ፎቶ ባንክ ይሂዱአሜሪካ ኢራንን መደብደቧ በአውሮፓ ህብረት እና በአሜሪካ መካከል ያለውን አለመግባባት ያሳያል ሲሉ የፈረንሳይ የአውሮፓ ፓርላማ አባል ተናገሩ
አሜሪካ ኢራንን መደብደቧ በአውሮፓ ህብረት እና በአሜሪካ መካከል ያለውን አለመግባባት ያሳያል ሲሉ የፈረንሳይ የአውሮፓ ፓርላማ አባል ተናገሩ - Sputnik አፍሪካ, 1920, 24.06.2025
ሰብስክራይብ

አሜሪካ ኢራንን መደብደቧ በአውሮፓ ህብረት እና በአሜሪካ መካከል ያለውን አለመግባባት ያሳያል ሲሉ የፈረንሳይ የአውሮፓ ፓርላማ አባል ተናገሩ

"ትራምፕ ኢራንን በቦምብ ለመምታት ሲወስኑ አውሮፓ ድርድሩ እንዲቀጥል አጥብቆ ጠይቆ ነበር" ሲሉ ቲዬሪ ማሪያኒ ለስፑትኒክ ተናግረዋል።

መጪው የኔቶ ጉባኤ በትራምፕ እና በአውሮፓ ህብረት መካከል እየሰፋ የመጣውን ልዩነት በጉልህ ያሳያል ሲሉ ጠቁመዋል።

ማሪያኒ አክለውም "ትራምፕ በአቋማቸው ከቀጠሉ አውሮፓ ህብረት ተጨማሪ ወታደራዊ ወጪዎችን ማለትም ተጨማሪ የአሜሪካ መሳሪያዎችን እንዲገዛ እንደገና መጠየቃቸው አይቀርም" ብለዋል።

የኔቶ ዋና ፀሐፊ ማርክ ሩተ የህብረቱ አባላት ከኢራን ጋር የድርድር ጥሪ ያቀርባሉ ሲሉ ቀደም ብለው የተናገሩ ሲሆን የፈረንሳዩ ፕሬዝዳንት ኢማኑኤል ማክሮን በበኩላቸው አሜሪካ በኢራን ላይ የፈፀመችውን ጥቃት "ሕገ-ወጥ" ሲሉ ጠርተውታል።

በእንግሊዘኛ ያንብቡ

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X

አዳዲስ ዜናዎች
0