- Sputnik አፍሪካ, 1920
Sovereignty Sources
ዓለም በሉላዊነት ምክንያት ስትተሳሰር ፤ ፕሮግራሙም አፍሪካ ባላት እምቅ የተፈጥሮ ኃብት፣ በማደግ ላይ ባለው የሕዝብ ቁጥሯ ፣ በወጣት ኃይሏ እና በአህጉሪቱ ባሉ አዳዲስ ግኝቶችና የመፍትሄ ሃሳቦች ያላትን የመወዳደር አቅምና ጥቅም በሰፊው ይዳስሳል፡፡ እንኳን ወደ 'ሶቨርኒቲ ሶርስ' ፕሮግራም በደህና መጡ፣

የመዳን ምዕተ- ዓመታት፦ የሩሲያ ቀይ መስቀል  የኢትዮ ሩሲያን ግንኙነት እንዴት አጠናከረው?

የመዳን ምዕተ- ዓመታት፦ የሩሲያ ቀይ መስቀል  የኢትዮ ሩሲያን ግንኙነት እንዴት አጠናከረው ?
ሰብስክራይብ
የቀይ መስቀል እና የቀይ ጨረቃ ንቅናቄ እንዲጀመር ምክንያት የሆነው እ.ኤ.አ ሰኔ 24 ቀን 1859 ፤ በሰሜን ኢጣሊያ ለንግድ ሥራ ሲጓዝ የነበረው አንሪ ዱና በጣሊያን ሶልፈሪኖ የተመለከተው አሰቃቂ እና ደም አፋሳሽ ጦርነት ነበር። ክስተቱ ዓለም አቀፍ የርህራሄ መልክን ፈጥሮ አልፏል።
ዛሬ የሶቨርኒቲ ሶርስስ ዝግጅታችን ይህንኑ ዕለት ሲያስብ ፣ የደጃዝማች ባልቻ የሩሲያ ቀይ መስቀል ሆስፒታል ሜዲካል ዳይሬክተር ዶ/ር አንድሬይ ቭላድሚሮቪች ጎንቻሮቭን በእንግድነት ጋብዟቸዋል።
የሩሲያ ቀይ መስቀል በህክምና ትብብር በኢትዮጵያ እና በሩሲያ መካከል ከ10ዐ ዓመታት በላይ የሰብዓዊ ዲፕሎማሲ ድልድይ ሆኖ ቆይቷል።
ዶ/ር አንድሬ ስለዚሁ ሆስፒታል የታሪካዊ ትስስር ህያው ምስክርነት አጽንኦት ሰጥተዋል፦
ሆስፒታሉ የሩሲያ እና ኢትዮጵያ ግንኙነት መሰረት ነው። የቀድሞውን አሻራ ለመጠበቅና ለማሳደግ ከሀገር እስከ [ግለሰብ] ለአጋርነትን በራችን ሁሌም ክፍት ነው ፣ ብለዋል።
ኢትዮጵያ በ2024 የብሪክስ አባል ሀገር መሆኗን ተከትሎም ፣ ለአጋርነቱ አዲስ መነቃቃት ፈጥሮለታል። ዶ/ር አንድሬ የሩሲያ ሰብዓዊ ድጋፍ ለሌሎች ትብብሮችም መሰረት ሆኗል ይላሉ።
እኛ ስለ ፖለቲካ ወይም ኢኮኖሚ አይደለም [እዚህ ያለነው] - ሕክምና እና ለጤና እንክብካቤ እንጂ ፤ ስራችን ግን ለበርካታ ትብብር መንገድ ይከፍታል ፣ ሲሉ ተናግረዋል።
ሙሉ መረጃውን ለማግኘት የሶቨርኒቲ ሶርስስ ፕሮግራምን ይከታተሉ።
ለማድመጥ ዝግጁ ከሆኑ...
አዳዲስ ዜናዎች
0