በእስራኤል ጥቃቶች የተገደሉ ኢራናውያን የኒውክሌር ሳይንቲስቶች እና ቤተሰቦቻቸው
16:33 24.06.2025 (የተሻሻለ: 16:54 24.06.2025)

© telegram sputnik_ethiopia
/ ሰብስክራይብ
በእስራኤል ጥቃቶች የተገደሉ ኢራናውያን የኒውክሌር ሳይንቲስቶች እና ቤተሰቦቻቸው
▪ ሰዲጊ ሳበር ዛሬ ጠዋት በጊላን በተፈፀመ ጥቃት የተገደለ ሲሆን ከጥቂት ቀናት በፊት የ17 ዓመቱ ልጁ ሞሐመድ ረዛ ሰዲቂ ሳበር እስራኤል ቴህራን በሚገኝ መንሪያ ቤት ላይ ባደረገችው ጥቃት ተገድሎ ነበር።
▪ ኢሳር ታባታባኢ ቆምሸህ ታዋቂ የኒውክሌር ሳይንቲስት ሲሆኑ ከባለቤታቸው መንሱሬህ ሀጂ ሳሌም ጋር ሰኔ 14 በቤታቸው ላይ በተፈፀመ ጥቃት ተገድለዋል።
▪ሰይድ ሙስጠፋ ሰዳቲ-አርማኪ ከነቤተሰቦቻቸው በእስራኤል ጥቃት ተገድለዋል፤ ከሟቾቹ መካከል የስምንት እና የአስራ አምስት ዓመት ሴት ልጆቻቸው እና የአምስት ዓመት ወንድ ልጃቸው ይገኙበታል።
▪ አሊ ባኩኢ ከማዛንዳራን የተገኙት የኒውክሌር ሳይንቲስት እና ቤተሰቦቻቸው ሰኔ 8 በተፈፀመ እስራኤል ጥቃት ተገድለዋል።
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X