ኢራን እስራኤልን እንዳጠቃች ወይም ለማጥቃት እንደተዘጋጀች የሚያረጋግጥ አንድም እውነታ የለም የለም ሲሉ ሰርጌ ላቭሮቭ አስታወቁ
14:33 24.06.2025 (የተሻሻለ: 14:54 24.06.2025)
© telegram sputnik_ethiopia
/ ሰብስክራይብ
ኢራን እስራኤልን እንዳጠቃች ወይም ለማጥቃት እንደተዘጋጀች የሚያረጋግጥ አንድም እውነታ የለም የለም ሲሉ ሰርጌ ላቭሮቭ አስታወቁ
የሩሲያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር በፕሪማኮቭ ንባብ ዓለም አቀፍ ጉባኤ ላይ ስለ ኢራን እና እስራኤል ግጭት የሰጡት መግለጫ ዋና ዋና ነጥቦች፦
🟠 አውሮፓውያን አሜሪካ እና እስራኤል በኢራን የኒውክሌር ተቋማት ላይ ለፈፀሙት ጥቃት በከፊል ተጠያቂ ናቸው፡፡
🟠 ሩሲያ ከአሜሪካ፣ ከኢራን እና ከእስራኤል ጋር ባላት መተማመንን መሠረት ግጭቱን ለመፍታት ሃሳብ አቅርባለች፡፡
🟠 ሞስኮ ግጭቱን ለመፍታት በሚደረገው ጥረት ለመሳተፍ ዝግጁ ናት፤ ሆኖም ገላጋይ ካልሆንኩ ብላ አትልም፡፡
🟠 የተኩስ አቁሙን ዘላቂነት አስመልክቶ ትክክለኛ መደምደሚያ ላይ መድረስ አሁንም አስቸጋሪ ነው።
ከአሜሪካ ጋር ስላለው ግንኙነት፦
🟠 በሞስኮ እና በዋሽንግተን መካከል ያለውን ግንኙነት የማረጋጋት ሂደት ቀላል አይደለም፤ ነገር ግን ዓለም አቀፍ ቀውሶችን ለመከላከል ጠቃሚ ሊሆን ይችላል፡፡
🟠 ሩሲያ እና ዩናይትድ ስቴትስ በስትራቴጂካዊ የመረጋጋት ጉዳዮች ላይ ትርጉም ያለው ውይይት ማድረግ አልቻሉም።
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X