ኢትዮጵያ የከርሰ ምድር ጥናት ሥልጠና ለሱዳናውያን ባለሙያዎች ሰጠች
13:43 24.06.2025 (የተሻሻለ: 14:04 24.06.2025)

© telegram sputnik_ethiopia
/ ሰብስክራይብ
ኢትዮጵያ የከርሰ ምድር ጥናት ሥልጠና ለሱዳናውያን ባለሙያዎች ሰጠች
ሥልጠናው በኢትዮጵያ ውሃ ቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩት አዘጋጅነት እንደተሠጠ የውሃና ኢነርጂ ሚኒስቴር አስታውቋል።
በመርሃ-ግብሩ ማስጀመሪያ በውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የአፍሪካ ጉዳዮች ምክትል ዋና ዳይሬክተር አምባሳደር መለስ አለም በከርሰ ምድር ውሃ ምርምር ቁፋሮ ኢትዮጵያ በአቅም ግንባታ ዘርፉ ለአፍሪካ ወንድሞች ሥልጠና መስጠቷ መልካም ጅምር መሆኑን ተናግረዋል።
የንድፍ -ሃሳብ እና የመስክ ላይ የተግባር ልምምዶችን ያጣመረው ሥልጠናው፦
🟠የከርሰ ምድር ውሃ ፍለጋ፣
🟠የውሃ ቁፋሮ ምህንድስና እና
🟠የውሃ ጉድጓድ ምርመራን ያካትታል።
ተቋሙ ከዚህ በፊት ለ18 የአፍሪካ ሀገራት አለም አቀፍ ደረጃውን የጠበቀ ስልጠና መሰጠቱ ተገልጿል።
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X

© telegram sputnik_ethiopia
/