#viral| በድሬዳዋ ፖሊስ ጣቢያ ገብቶ የፖሊስ ያለ ያለው ጅብ!
11:09 24.06.2025 (የተሻሻለ: 11:24 24.06.2025)
© telegram sputnik_ethiopia
/ ሰብስክራይብ
#viral| በድሬዳዋ ፖሊስ ጣቢያ ገብቶ የፖሊስ ያለ ያለው ጅብ!
በድሬዳዋ ከተማ ሰባተኛ እየተባለ በሚጠራው አካባቢ ትናንት አንድ የነጋበት ጅብ የአካባቢውን ማሕበረስብ በማስደነገጡ ተሰባስበው በዱላ፣ ድንጋይ እና ሌሎች ነገሮች ድብደባ እንዳደረሱበት የከተማዋ ፖሊስ በማሕበራዊ ገፁ ባጋራው መረጃ ገልጿል፡፡
ድብደባውን መቋቋም የከበደው ጅብ ህይወቱን ለማትረፍ ሳቢያን በተሰኘው አካባቢ በሚገኝ የፖሊስ ጣቢያ ቢሮ ሰተት ብሎ በመግባት እንደተደበቀ ተገልጿል፡፡
ፖሊስ ማህበረሰብን ካረጋጋ በሗላ ከዱር እንሰሳ ጥበቃ ጋር በመወያየት ጅቡን ማህበረሰቡን በማይጎዳ መልኩ ወደ ጫካ እንደለቀቅ አስታውቋል።
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X