በኳታር የአሜሪካ ጦር ሰፈር ላይ የደረሰውን ጥቃት ተከትሎ የኢራን ጦር የሰጠው መግለጫ
20:57 23.06.2025 (የተሻሻለ: 21:04 23.06.2025)

© telegram sputnik_ethiopia
/ ሰብስክራይብ
በኳታር የአሜሪካ ጦር ሰፈር ላይ የደረሰውን ጥቃት ተከትሎ የኢራን ጦር የሰጠው መግለጫ
▪ የዩናይትድ ስቴትስ ወንጀለኛ አገዛዝ በኢራን እስላማዊ ሪፐብሊክ ሰላማዊ የኒውክሌር ተቋማት ላይ ያደረሰውን አፀያፊ ወታደራዊ ጥቃት እና የዓለም አቀፍ ሕግጋትን በግልፅ መጣሱን ተከትሎ የእስላማዊ አብዮታዊ ዘብ በኳታር አል ኡዴድ የጦር ሠፈር ላይ አድቃቂ እና ከባድ የሚሳኤል ጥቃት ፈጽሟል።
▪ ይህ የጦር ሰፈር የአሜሪካ አየር ኃይል ዋና መሠረት እና በምዕራብ እስያ ቀጣና የአሜሪካ አሸባሪ ጦር ትልቁ ስትራቴጂካዊ ቦታ ነው።
▪ በዚህ ጥቃት ጥቅም ላይ የዋሉት ሚሳኤሎች በኢራን ሰላማዊ የኒውክሌር ተቋማት ላይ በአሜሪካ ጦር ከተጣሉት ቦምቦች ጋር ተመጣጣኝ ናቸው።
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X