የአል-ሸባብ ታጣቂዎች ከደቡብ ሶማሊያ ቁልፍ ይዞታ ተነቀሉ
19:58 23.06.2025 (የተሻሻለ: 20:04 23.06.2025)

© telegram sputnik_ethiopia
/ ሰብስክራይብ
የአል-ሸባብ ታጣቂዎች ከደቡብ ሶማሊያ ቁልፍ ይዞታ ተነቀሉ
የአፍሪካ ሕብረት የድጋፍ እና ማረጋጋት ተልዕኮ (አውሶም) እና የሶማሊያ ብሔራዊ ጦር ኃይሎች በጋራ ባካሄዱት "ኦፕሬሽን ሳይለንት ስቶርም" የተሰኘ ዘመቻ ስልታዊ ጠቀሜታ ያላቸውን የሳቢድ እና የአኖሌ መንደሮችን ከአል-ሻባብ* አስለቅቀዋል።
ለሶስት ቀናት የተካሄደው ዘመቻ አሸባሪዎች ጥቃት ለማቀድ እና ከአካባቢው ነዋሪዎች ገንዘብ ለመበዝበዝ የሚጠቀሙባቸውን ቁልፍ ቦታዎች ሰብሯል።
"ሳቢድ እና አኖሌ አሸባሪዎች አሰቃቂ ጥቃቶችን የሚያቅዱበት ስልታዊ ቦታ ሆኖ ቆይቷል" ሲሉ የአውሶም ሴክተር አንድ አዛዥ ጆሴፍ ሴሙዋንጋ ተናግረዋል።
በርካታ አሸባሪዎች ከተደመሰሱ እና ከፍተኛ መጠን ያለው ጥይት ከተያዘ በኋላ ጥምር ኃይሎቹ አካባቢውን ማስጠበቅ እና ወደ መካከለኛው ሸበሌ መግፋት ላይ አተኩረዋል።
የአውሶም አባል የሆኑት ሳም ካቩማ "የሶማሊያ የሽግግር እቅድን ለመተግበር ሙሉ በሙሉ ቁርጠኞች ነን" ሲሉ በድጋሚ አረጋግጠዋል።
*በሩሲያ እና በበርካታ ሀገራት በሕገ-ወጥነት የተፈረጀ የሽብር ድርጅት
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X
© telegram sputnik_ethiopia / ወደ ፎቶ ባንክ ይሂዱ

© telegram sputnik_ethiopia / ወደ ፎቶ ባንክ ይሂዱ

© telegram sputnik_ethiopia / ወደ ፎቶ ባንክ ይሂዱ

© telegram sputnik_ethiopia / ወደ ፎቶ ባንክ ይሂዱ
