ብሪክስ የአፍሪካ ሀገራት የወደፊት ዕጣ ፈንታቸውንና የጋራ የትግል አጋራቸውን እንዲመርጡ ዕድል መፍጠሩን የታንዛኒያ ባለሥልጣን ገለፁ

© telegram sputnik_ethiopia / ወደ ፎቶ ባንክ ይሂዱብሪክስ የአፍሪካ ሀገራት የወደፊት ዕጣ ፈንታቸውንና የጋራ የትግል አጋራቸውን እንዲመርጡ ዕድል መፍጠሩን የታንዛኒያ ባለሥልጣን ገለፁ
ብሪክስ የአፍሪካ ሀገራት የወደፊት ዕጣ ፈንታቸውንና የጋራ የትግል አጋራቸውን እንዲመርጡ ዕድል መፍጠሩን የታንዛኒያ ባለሥልጣን ገለፁ - Sputnik አፍሪካ, 1920, 23.06.2025
ሰብስክራይብ

ብሪክስ የአፍሪካ ሀገራት የወደፊት ዕጣ ፈንታቸውንና የጋራ የትግል አጋራቸውን እንዲመርጡ ዕድል መፍጠሩን የታንዛኒያ ባለሥልጣን ገለፁ

ብሪክስ የአፍሪካ ሀገራት የራሳቸውን ፍላጎት እና ተፅዕኖ የሚያሳርፉበት ዓለም አቀፍ ዕድል መፍጠሩን በታንዛኒያ ፕሬዝዳንት ፅህፈት ቤት የሕዝብ አገልግሎት እና መልካም አስተዳደር ባለሙያ ሮምዋርድ ዲኦኒዚ ራዋማሉምባ ከአስረኛው የአፍሪካ የሕዝብ አገልግሎት ቀን ጎን ለጎን ለስፑትኒክ አፍሪካ ተናግረዋል፡፡

“የብሪክስ መምጣት አፍሪካውያን ለጋራ ግብ፣ አመለካከት፣ ለጋራ መጪ ግዜና ለጋራ ትግል ከማን ጋር መሰለፍ እንዳለባቸው እንዲያዩ እድል ሰጥቷል” ብለዋል፡፡

ለውጦችና ውሳኔዎች ላይ ተፅዕኖ እንዲኖርን እንፈልጋለን ስንል ምዕራባውያንን ለማደናቅፍ ሳይሆን፤ የአፍሪካ እና ሌሎች የዓለም ክፍሎች ምርጫ እንዲጠበቅ ካለን ፍላጎት አንፃር ነው ሲሉ አስረድተዋል።

ራዋማሉምባ የብሪክስ ሀገራት የተፈጥሮ ሀብት፣ የሰው ኃይል እና ቴክኖሎጂ እንዳላቸው በመጥቀስ፤ እነዚህን ሀብቶች በጋራ በመጠቀም በምዕራባውያን እና የዓለም ፖለቲካ ላይ ተፅዕኖ ማሳዳር እንደሚችሉ አብራርተዋል፡፡

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X

አዳዲስ ዜናዎች
0