ግልገል ጊቤ ሦስት 7 ሺህ ጊጋ ዋት ሰዓት የኤሌክትሪክ ኃይል ማመንጨቱ ተገለፀ
17:44 23.06.2025 (የተሻሻለ: 18:04 23.06.2025)

© telegram sputnik_ethiopia
/ ሰብስክራይብ
ግልገል ጊቤ ሦስት 7 ሺህ ጊጋ ዋት ሰዓት የኤሌክትሪክ ኃይል ማመንጨቱ ተገለፀ
ግድቡ በኢትዮጵያ የኤሌክትሪክ ኃይል አቅርቦት ላይ ከፍተኛውን ድርሻ በመያዝ ለሀገሪቱ ኢኮኖሚ አዎንታዊ ሚና እየተወጣ ይገኛል ተብሏል፡፡
የኃይል ማመንጫው የሀገሪቱን የኃይል አቅርቦት 50 በመቶ እንደሸፈነና ለቀጣናው ሀገራት የኤሌክትሪክ ኃይል በማቅረብ ትልቅ አስተዋጽኦ እያበረከተ መሆኑን የግድቡ ሥራ አስፈፃሚ ሃብታሙ ሰሙን ጠቅሶ የሀገር ውስጥ ሚዲያ ዘግቧል፡፡
ከታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ ቀጥሎ ግዙፉ የሀገሪቷ የኃይል ማመንጫ፤ ከ1 ሺህ 870 ሜጋ ዋት በላይ የኤሌክትሪክ የማመንጨት አቅም አለው ተብሏል፡፡
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X