የኢትዮጵያ ልዩ የኢኮኖሚ ዞኖች በበጀት ዓመቱ 900 ሚሊየን ዶላር ኢንቨስትመንት መሳባቸው ተገለፀ
14:49 23.06.2025 (የተሻሻለ: 15:04 23.06.2025)
© telegram sputnik_ethiopia / ወደ ፎቶ ባንክ ይሂዱየኢትዮጵያ ልዩ የኢኮኖሚ ዞኖች በበጀት ዓመቱ 900 ሚሊየን ዶላር ኢንቨስትመንት መሳባቸው ተገለፀ

© telegram sputnik_ethiopia
/ ሰብስክራይብ
የኢትዮጵያ ልዩ የኢኮኖሚ ዞኖች በበጀት ዓመቱ 900 ሚሊየን ዶላር ኢንቨስትመንት መሳባቸው ተገለፀ
በሀገሪቱ 13 ልዩ የኢኮኖሚ ዞኖች የሚገኙ ሲሆን በአሁኑ ሰዓት 89% የሚሆኑት በኢንቨስተሮች ተይዘዋል፡፡
🟠የቦሌ ለሚና የአዳማ ኢንዱስትሪ ፓርኮች 100%፣
🟠የጅማ ልዩ የኢኮኖሚ ዞን 9ዐ% ተይዘዋል።
ለእድገቱ የኢንቨስተሮችን ውጣ ውረድ ያስወገዱ እና የተሻለ የኢንቨስትመንት ምህዳር የፈጠሩ 80 የሚጠጉ የፖሊሲ ማሻሻያዎች መደረጋቸው ምክንያት እንደሆኑ በኢንዱስትሪ ፓርኮች ልማት ኮርፖሬሽን የኢንቨስትመንት ፕሮሞሽንና ማርኬቲንግ ዘርፍ ሥራ አስፈፃሚ ዘመን ጁነዲ ተናግረዋል፡፡
በልዩ የኢኮኖሚ ዞኖች ውስጥ ከጥቂት ዓመታት በፊት ከ5% በታች የነበረው የሀገር ውስጥ ኢንቨስተሮች ተሳትፎ አሁን ላይ 60% ደርሷል ማለታቸውን የሀገር ውስጥ ጋዜጣ ዘግቧል፡፡
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X