በኢራን- እስራኤል ውጥረት ዙሪያ ሰኞ ረፋድ የተሠሙ ጉዳዮች፦
በኢራን- እስራኤል ውጥረት ዙሪያ ሰኞ ረፋድ የተሠሙ ጉዳዮች፦
◾ የእስራኤል ጦር በምዕራብ፣ በምስራቅ እና በመካከለኛው ኢራን በሚገኙ ስድስት የአየር ማረፊያዎች ላይ ጥቃት መሰንዘሩን እና 15 የውጊያ አውሮፕላኖችን እና ሄሊኮፕተሮችን ማውደሙን አስታውቋል።
◾ እስራኤል የሽንፈት አፋፍ ላይ ባትሆን ኖሮ አሜሪካ በመካከለኛው ምስራቅ ግጭት ውስጥ ጣልቃ አትገባም ነበር ሲሉ በጀርመን የቀድሞ የኢራን አምባሳደር ለስፑትኒክ ተናግረዋል።
◾ ዶናልድ ትራምፕ የኢራንን የኒውክሌር ተቋማት በመደብደብ ዲፕሎማሲን አምክነዋል ሲሉ የቀድሞው ዲፕሎማት አክለዋል።
◾ ትራምፕ የአሜሪካ ጦር የኢራን የኒውክሌር ተቋማትን ማውደሙን አስረግጠው፤ "መደምሰስ" የሚለው ቃል የጥቃቱን መጠን በትክክል ይገልፀዋል ሲሉ ተናግረዋል።
◾ ትራምፕ የኢራን አመራር "ኢራንን እንደገና ታላቅ ማድረግ" አይችልም በማለት፤ "የስርዓት ለውጥ" ሃሳብ አቅርበዋል።
◾ የተባበሩት ዓረብ ኤምሬቶች ፕሬዝዳንት ሞሐመድ ቢን ዛይድ ከኦማን ሱልጣን ሃይተም ቢን ታሪክ፣ ከፈረንሳዩ ማክሮን እና ከጣሊያን ጠቅላይ ሚኒስትር ሜሎኒ ጋር ባደረጉት የስልክ ውይይቶች በኢራን ዙሪያ ያለውን ሁኔታ አንስተዋል ሲሉ የአረብ ኤሚሬቶች መገናኛ ብዙኃን ዘግበዋል።
◾ ኢራን የሆርሙዝ የባሕር ወሽመጥን ከዘጋች አሜሪካን ጨምሮ ከነዳጅ ቀውስ ማንም አያመልጥም ሲሉ የሩሲያ ልዩ መልዕክተኛ ኪሪል ዲሚትሪየቭ ተናግረዋል።
◾ ኢራን ከአሜሪካ ጥቃት ቀናት በፊት ከፎርዶው የኒውክሌር ተቋም መሳሪያዎችን እና ዩራኒየሟን ማስወጣቷን አንድ የአሜሪካ ጋዜጣ ሁለት የእስራኤል ባለሥልጣናትን በመጥቀስ ዘግቧል።
◾ እስራኤል በኢራን ላይ ለሚሰነዘር ጥቃት እየተዘጋጀች እያለች ዓለም አቀፉን ማህበረሰብ ለማሳሳት ዲፕሎማሲን ተጠቅማለች ሲሉ የኢራን የተመድ ልዑክ ተናግረዋል።
◾ ሩሲያ የእስራኤል እና የአሜሪካ የጥቃት እርምጃዎች በአስቸኳይ እንዲቆሙ ታሳስባለች ያሉት በተመድ የሩሲያ ልዑክ፤ አሜሪካ "የፓንዶራ ሳጥንን" ከፍታ ሊከተል የሚችለውን የጥፋት መጠን መተንበይ የሚችል የለም ብለዋል፡፡
◾ የኢራን የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አባስ አራግቺ ከሩሲያ አመራሮች ጋር ለመነጋገር ሞስኮ መድረሳቸውን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ ዛካሮቫ አረጋግጠዋል።
◾ ቴህራን የመካከለኛው ምስራቅ ግጭትን በተመለከተ ሩሲያ በኢራን ላይ የሚሰነዘሩ ጥቃቶችን ማውገዟን ታደንቃለች ሲሉ አራግቺ ተናግረዋል።
◾ በሩሲያ እና በአሜሪካ መካከል ያለው ግንኙነት በኢራን ጉዳይ ላይ ጨምሮ እየቀጠለ ነው ሲሉ የክሬምሊን ረዳት ዩሪ ኡሻኮቭ ተናግረዋል።
ከማህበራዊ የትስስር ገፆች የተገኙ ምሥሎች በዛሬው ዕለት ምዕራብ ኢራን በምትገኘው ኬርማንሻህ ከተማ ላይ የተፈፀመውን የእስራኤል ጥቃት ያሳያሉ።
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X