እስራኤል ኢራንን ለመደብደብ የምትሰጠውን መሠረተ ቢስ 'ሰበብ' ትታ ሰላምን መምረጥ አለባት ሲሉ የደቡብ አፍሪካ ምክትል ፕሬዝዳንት ተናገሩ

ሰብስክራይብ

እስራኤል ኢራንን ለመደብደብ የምትሰጠውን መሠረተ ቢስ 'ሰበብ' ትታ ሰላምን መምረጥ አለባት ሲሉ የደቡብ አፍሪካ ምክትል ፕሬዝዳንት ተናገሩ

ፕሪቶሪያ የእስራኤል-ፍልስጤም እና የእስራኤል-ኢራን ውጥረቶችን ጨምሮ ሁልጊዜም ሰላማዊ የግጭት መፍቻ መንገዶችን ትደግፋለች። ምክንያቱም ኃይል ውጥረትን ያባብሳል ሲሉ ፖል ማሻቲሌ ለስፑትኒክ አፍሪካ ተናግረዋል።

"ምክንያቱ ምንም ይሁን ምን፤ አንድ ሀገር ሌላን ሀገርን በቀላሉ ማጥቃት የሚችልበት መንገድ መኖር የለበትም" ሲሉ ምክትል ፕሬዝዳንቱ አስረግጠዋል።

እስራኤል ኢራን የኒውክሌር ጦር መሳሪያ እየሠራች እንደሆነ ከጠረጠረች መላክ የነበረባት ባምቦችን ሳይሆን ተቆጣጣሪዎችን ነው ሲሉ ባለሥልጣኑ ተናግረዋል።

ሰላም ዓለም አቀፍ ድርጊቶችን እንዴት መምራት እንዳለበት ምክትል ፕሬዝዳንቱ የገለፁትን አቋም ለመስማት ቪዲዮውን ይመልከቱ!

በእንግሊዘኛ ያንብቡ

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X

አዳዲስ ዜናዎች
0