የሩሲያ-አፍሪካ ግንኙነት ከንግድ ባለፈ ወደ ቴክኖሎጂ አጋርነቶችና የጋራ ኢንተርፕራይዞች የሚሸጋገርበት ጊዜ አሁን ነው ሲሉ የሩሲያ ባለሥልጣን ተናገሩ
18:36 22.06.2025 (የተሻሻለ: 18:54 22.06.2025)
© telegram sputnik_ethiopia / ወደ ፎቶ ባንክ ይሂዱየሩሲያ-አፍሪካ ግንኙነት ከንግድ ባለፈ ወደ ቴክኖሎጂ አጋርነቶችና የጋራ ኢንተርፕራይዞች የሚሸጋገርበት ጊዜ አሁን ነው ሲሉ የሩሲያ ባለሥልጣን ተናገሩ

© telegram sputnik_ethiopia
/ ሰብስክራይብ
የሩሲያ-አፍሪካ ግንኙነት ከንግድ ባለፈ ወደ ቴክኖሎጂ አጋርነቶችና የጋራ ኢንተርፕራይዞች የሚሸጋገርበት ጊዜ አሁን ነው ሲሉ የሩሲያ ባለሥልጣን ተናገሩ
የሩሲያ ፌዴሬሽን ምክር ቤት (ስቴት ዱማ) ምክትል አፈ-ጉባኤ አሌክሳንደር ባባኮቭ ለሩሲያ ሚዲያ በሰጡት ቃል በ #SPIEF2025 ሩሲያ ከአፍሪካ ጋር በመተባበር ምን ሊሳካ እንደሚችል አሳይታለች ብለዋል።
"ለትብብር የተመረጠ አቀራረብ አንከተልም በሚል አረዳድ በጋራ ወደፊት መንቀሳቀስ አለብን። የአፍሪካ ሀገራትን እንደ እኩል አጋሮቻችን ነው የምናያቸው" ሲሉ ባለሥልጣኑ አስረድተዋል።
በርካታ በፎረሙ የተሳተፉ የአፍሪካ ልዑካን ቡድኖች በፓርላማ ሆነ በመንግሥታት ደረጃ ከሩሲያ ጋር ያለው ግንኙነት እድገት እያሳየ በመምጣቱ የተሰማቸውን እርካታ መግለጻቸውንም ጠቁመዋል።
የ2025 የሴንት ፒተርስበርግ ዓለም አቀፍ የኢኮኖሚ ፎረም ከ144 ሀገራት የተውጣጡ ልዑካን ቡድኖች እንደተሳተፉበት አዘጋጅ ኮሚቴው አስታውቋል።
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X