ሩሲያ አሜሪካ በኢራን ላይ የፈፀመችውን ጥቃት “ኃላፊነት የጎደለው” ስትል ነቀፈች
18:18 22.06.2025 (የተሻሻለ: 18:34 22.06.2025)

© telegram sputnik_ethiopia
/ ሰብስክራይብ
ሩሲያ አሜሪካ በኢራን ላይ የፈፀመችውን ጥቃት “ኃላፊነት የጎደለው” ስትል ነቀፈች
ዋሽንግተን “ዓለም አቀፍ ሕግን እና የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ቻርተርን በግልጽ የጣሰ” እርምጃ ወስዳለች ሲል የሩሲያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ባወጣው መግለጫ አጽንዖት ሰጥቷል።
"ድርጊቱ ያስከተላቸው መዘዞች የጨረር ጉዳቶችን ጨምሮ የሚታዩ ይሆናል። ይሁን እንጂ ጥቃቱ በክልሉ እና በዓለም አቀፍ ደረጃ ደህንነትን የበለጠ ሊያናጋ የሚችል አደገኛ ውጥረት መፈጠሩን ማረጋገጫ ሰጥቷል” ሲል አክሏል።
እነዚህ ጥቃቶች፦
የኒውክሌር ጦር መሳሪያ ያለማስፋፋት ስምምነትን (ኢራን ፈራሚ ናት) እና
የዓለም አቀፉ የኒውክሌር ተቆጣጣሪ ኤጄንሲን የክትትል እና ማረጋጋጫ ሂደት አበላሽተዋል።
“የተመድ የፀጥታው ምክር ቤት ጠንኳራ አቋም መውሰድ እንዳለበት ግልፅ ነው። በዩናይትድ ስቴትስ እና በእስራኤል የሚወሰዱ ግጭት ቀስቃሽ እና አለመረጋጋት የሚፈጥሩ ድርጊቶች በጋራ ውድቅ መደረግ አለባቸው” ሲል የሩሲያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ደምድሟል።
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X