ሩሲያ አሁንም ወሳኝ የዓለም አቀፍ ትስስር ማዕከል ናት ሲሉ የፈረንሳይ ስፖርት ወኪል ተናገሩ

ሰብስክራይብ

ሩሲያ አሁንም ወሳኝ የዓለም አቀፍ ትስስር ማዕከል ናት ሲሉ የፈረንሳይ ስፖርት ወኪል ተናገሩ

"ምዕራባውያን መገናኛ ብዙኃን በየቀኑ በቴሌቪዥን ከሚሉት በተቃራኒ ሩሲያ በመላው ዓለም ከሚገኙ የተለያዩ አካላት ጋር የቆየ ትስስር አላት" ሲሉ የፊጂታል ፈረንሳይ ኃላፊ ጄረሚ ቦሂ ለስፑትኒክ አፍሪካ ተናግረዋል።

"ፈረንሳይ እና ሩሲያ በተለያዩ ደረጃዎች ፖለቲካዊ፣ የኢንዱስትሪ፣ የኢኮኖሚና ንግድ እንዲሁም ባሕላዊ እና ግላዊ ወዳጅነታቸውን ዘላቂና ጥልቅ በሆነ መንገድ አስቀጥለዋል" ሲሉ ከ #SPIEF2025 ፎረም ጎን ለጎን ተናግረዋል።

በተጨማሪም ምንም እንኳን የፖለቲካ ውጥረቶች ቢኖሩም ስፖርት አሁንም ሰዎችን የማቀራረብ ኃይል እንዳለው ገልጸዋል።

"እንደዚህ ዓይነት ውጥረቶች ከ100 ዓመታት በፊት በኦሎምፒክ ዘመን ሁሉ ነበሩ። ጦርነቶችና ግጭቶች ቢኖሩም ኦሎምፒክ ቀጥሏል። በተለይም በችግር ጊዜ ግንኙነቶችን እና ወዳጃዊ ትስስሮችን መገንባታችንን መቀጠል አለብን" ሲሉ ቦሂ አፅንዖት ሰጥተዋል።

በእንግሊዘኛ ያንብቡ

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X

አዳዲስ ዜናዎች
0