በሆርሙዝ የባሕር ወሽመጥ የሚፈጠር መስተጓጎል ከባድ መዘዝ እንደሚያመጣ ዚምባብዌያዊው ምሁር አስጠነቀቁ

© telegram sputnik_ethiopia / ወደ ፎቶ ባንክ ይሂዱበሆርሙዝ የባሕር ወሽመጥ የሚፈጠር መስተጓጎል ከባድ መዘዝ እንደሚያመጣ ዚምባብዌያዊው ምሁር አስጠነቀቁ
በሆርሙዝ የባሕር ወሽመጥ የሚፈጠር መስተጓጎል ከባድ መዘዝ እንደሚያመጣ ዚምባብዌያዊው ምሁር አስጠነቀቁ - Sputnik አፍሪካ, 1920, 22.06.2025
ሰብስክራይብ

በሆርሙዝ የባሕር ወሽመጥ የሚፈጠር መስተጓጎል ከባድ መዘዝ እንደሚያመጣ ዚምባብዌያዊው ምሁር አስጠነቀቁ

መካከለኛው ምሥራቅ ተጨማሪ ጦርነት ማስተናገድ አይችልም የሚሉት በዚምባብዌ ቢንዱራ ዩኒቨርስቲ የዓለም አቀፍ ግኑኝነት መምህር እና ተመራማሪ ሮናልድ ቺፔኬ ናቸው።

"አሜሪካ እና አይሲስ ኢራቅን ከወረሩ በኋላ የተፈጠረው ጥፋትና ሰብዓዊ ቀውስ ለሁሉም በግልፅ የታየ ነው። ብዙም ሳይርቅ አፍጋኒስታን ጦርነት ባስከተለው ውጤት አሁንም እየተንገዳገደች ነው። ሶሪያም በተመሳሳይ። ለግጭቱ መፍትሄ ለማምጣት ሁሉም መደረግ አለበት" ሲሉ ለስፑትኒክ አፍሪካ ተናግረዋል።

አክለውም በቀጣናው ወሳኝ በሆነው የሆርሙዝ መተላለፊያ የሚፈጠር መስተጓጎል የአፍሪካን በር እንደሚያንኳኳም ጠቁመዋል።

"የሆርሙዝን የባሕር ወሽመጥ አስፈላጊነት ከግምት ውስጥ በመክተት ኢኮኖሚያዊ ፈተናዎችን ሊቀሰቅስ ይችላል። ወሳኝ በሆነው የነዳጅ ማስተላለፊያ የሚከሰት ረብሻ በእርግጠኝነት ከባድ መዘዝ ያስከትላል። የነዳጅ ዋጋ ሊያሻቅብ ስለሚችል ከመካከለኛ ምስራቅ ነዳጅ የሚገዙ ሀገራት ሊጎዱ ይችላሉ። መጀመሪያውኑም ደካማ ኢኮኖሚ ያላቸው የአፍሪካ ሀገራት በተለየ መልኩ ይፈተናሉ" ሲሉ አብራርተዋል።

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X

አዳዲስ ዜናዎች
0