የኢራን አብዮታዊ ዘብ አሜሪካ ለፈፀመችው ጥቃት እንድትጸጸት እናደርጋለን በማለት ዛተ
15:08 22.06.2025 (የተሻሻለ: 15:24 22.06.2025)
© telegram sputnik_ethiopia
ሰብስክራይብ
የኢራን አብዮታዊ ዘብ አሜሪካ ለፈፀመችው ጥቃት እንድትጸጸት እናደርጋለን በማለት ዛተ
የዩናይትድ ስቴትስ ጥቃት ኢራን ራሷን የመከላከል ሕጋዊ መብቷን እንድትጠቀም እና ምላሽ እንድትሰጥ እንዲሁም አሜሪካ በድርጊቷ እንድትጸጸት ለማድረግ ሁሉንም አማራጮች እንድትጠቀም ያስችላታል ሲል የኢራን ብሄራዊ ማሰራጫ የአብዮታዊ ዘቡን መግለጫ ጠቅሶ ዘግቧል።
በመካከለኛው ምስራቅ የሚገኙ የአሜሪካ የጦር ሰፈሮች ቁጥር፣ ቦታ እና ስፋት የአሜሪካን ጥንካሬ ብቻ ሳይሆን ተጋላጭነቷን የሚጨምሩ ደካማ ጎኖቿ ናቸው ሲል መግለጫው አክሏል።
የኢራን አብዮታዊ ዘብ የእስራኤልን መሠረተ ልማቶች እና ስትራቴጂካዊ ጠቀሜታ ያላቸውን ተቋማት ማጥቃቱን እንደሚቀጥል ገልጿል።
በማህበራዊ የትስስር ገፆች የሚዘዋወሩ ምስሎች በቴል አቪቭ አካባቢ የኢራን ጥቃቶች ያስከተሉትን ጉዳቶች ያሳያሉ።
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X