አሜሪካ የኢራንን የኒውክሌር ተቋማት ትናንት ምሽት አጥቅታለች። እስከ ዛሬ ጠዋት የተሠሙ ቁልፍ ክስተቶች፦

© telegram sputnik_ethiopia / ወደ ፎቶ ባንክ ይሂዱአሜሪካ የኢራንን የኒውክሌር ተቋማት ትናንት ምሽት አጥቅታለች። እስከ ዛሬ ጠዋት የተሠሙ ቁልፍ ክስተቶች፦
አሜሪካ የኢራንን የኒውክሌር ተቋማት ትናንት ምሽት አጥቅታለች። እስከ ዛሬ ጠዋት የተሠሙ ቁልፍ ክስተቶች፦ - Sputnik አፍሪካ, 1920, 22.06.2025
ሰብስክራይብ

አሜሪካ የኢራንን የኒውክሌር ተቋማት ትናንት ምሽት አጥቅታለች። እስከ ዛሬ ጠዋት የተሠሙ ቁልፍ ክስተቶች፦

የአሜሪካ ወታደራዊ እርምጃ

▪የአሜሪካ ቦምብ ጣይ ጄቶች ቅዳሜ ከምሽቱ 5:00 ገደማ በኢራን የፎርዶውና ናታንዝ የኒውክሌር ተቋማት ላይ ጥቃት አድርሰዋል።

▪አሜሪካ ጥቃቶቹ መንግሥት ለመገልበጥ ያለሙ እንዳልሆኑ በቀጥታ ለኢራን ገልጻለች።

▪ትራምፕ ኢራን የሰላም ጥሪውን ካልተቀበለች  በድጋሚ ጥቃት ለመፈፀም ዝግጁ ነን ብለዋል።

የኢራን ምላሽ

▪ቴህራን በፎርዶው ጥቃት እንደሚሰነዘር በመጠበቅ ቁሳቁሶችን እንዳወጣችና ሊቀለበስ የማይችል ጉዳት እንዳልደረሰ ገልጻለች።

▪አሜሪካ ኢራን ላይ ጦርነት ከፍታለች ሲል የሀገሪቱ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር አስታውቋል።

▪ጥቃቱ እስራኤል ኢራን ላይ የፈፀመችውን ጥቃት በማቀድ አሜሪካ ተሳታፊ እንደነበረች ያሳያል ብሏል።

▪የአሜሪካ ጥቃት መጠነ ሰፊ መዘዞች እንደሚያስከትል የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ ገልጸዋል።

▪ኢራን አስቸኳይ የጸጥታው ምክር ቤት ስብሰባ ጠርታለች።

የጨረር ፍሰት፦ የኢራን አቶሚክ ኢነርጂ ድርጅት ምንም ዓይነት የጨረር ፍሰት እንዳልተከሰተ ያወጣውን መግለጫ ዓለም አቀፉ የአቶሚክ ኤጀንሲ አረጋግጧል።

የእስራኤል ምላሽ፦

▪ኔታንያሁ የኢራን ኒውክሌር አቅምን እንደሚያጠፉ የገቡት የቆየ ቃል መፈጸሙን ተናግረዋል።

▪ከአሜሪካ ጥቃት በሗላ እስራኤል የአየር ክልሏን ዘግታለች።

ዓለም አቀፍ ምላሽ፦

▪የተመድ ዋና ጸሃፊ ጥቃቱ የቀጣናውን ሁኔታ በማባባስ ለዓለም ሰላም ስጋት ሆኗል ሲሉ አውግዘዋል።

▪ሁቲዎች በቀይ ባሕር በአሜሪካ መርከቦች ላይ የበቀል ጥቃት ዛቻ አሰምተዋል።

▪ኢራቅና ሳዑዲ አረቢያ የአሜሪካን ጥቃት አውግዘዋል።

በእንግሊዘኛ ያንብቡ

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X

አዳዲስ ዜናዎች
0