ቴህራን ወደ ሰላም ካልመጣች አሜሪካ በድጋሚ ኢራን ላይ ጥቃት ለመፈፀም ዝግጁ ናት ሲሉ ትራምፕ ተናገሩ

ሰብስክራይብ

ቴህራን ወደ ሰላም ካልመጣች አሜሪካ በድጋሚ ኢራን ላይ ጥቃት ለመፈፀም ዝግጁ ናት ሲሉ ትራምፕ ተናገሩ

"ሰላም በፍጥነት ካልመጣ ሌሎች ተጨማሪ ኢላማዎችን በትክክል፣ በፍጥነት እና በብቃት እንመታለን። አብዛኛዎቹ በደቂቃዎች ውስጥ ሊደመሰሱ ይችላሉ" ሲሉ የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ አሜሪካ በኢራን የኒውክሌር ተቋማት ላይ የፈፀመችውን የምሽት ጥቃት ተከትሎ ለሕዝቡ ባደረጉት ንግግር ገልፀዋል።

የትራምፕ ቁልፍ መግለጫዎች፦

▪የኢራን ቁልፍ የኒውክሌር ማበልፀጊያ ተቋማት "ሙሉ በሙሉ ተደምስሰዋል።"

▪ተልዕኮው የኢራን የኒውክሌር ማበልፀጊያን አቅም ማጥፋት እና "የኒውክሌር ስጋትን ማስቆም" ነበር።

▪ዩናይትድ ስቴትስ በኢራን በጣም አስቸጋሪ የሆኑትን ኢላማዎች ብትመታም "በርካታ ኢላማዎች ይቀራሉ።"

▪ዩናይትድ ስቴትስ ተመሳሳይ ጥቃት እንደማትፈፅም ተስፋ ታደርጋለች።

▪"ኢራን ሰላም አሊያም ከእስካሁኑ የባሰ ጥፋት ይጠብቃታል።"

▪"የወደፊት ጥቃቶች በጣም የከፉ እና በጣም ቀላል ሊሆኑ ይችላሉ።"

በእንግሊዘኛ ያንብቡ

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X

አዳዲስ ዜናዎች
0