"ኢትዮጵያ እና ብራዚል የዓለም የምግብ ደህንነት ተግዳሮቶችን ለመቅረፍ በጋራ ይሠራሉ"
20:07 21.06.2025 (የተሻሻለ: 20:24 21.06.2025)

© telegram sputnik_ethiopia
/ ሰብስክራይብ
"ኢትዮጵያ እና ብራዚል የዓለም የምግብ ደህንነት ተግዳሮቶችን ለመቅረፍ በጋራ ይሠራሉ"
ረሃብና ድርቅን ለመቋቋም አፍሪካና እና የደቡባዊ ዓለም ሀገራት በትብብር የሚሠሩበት ጊዜ አሁን ነው ሲሉ የብራዚል ግብርና እና የእንስሳት እርባታ ምክትል ሚኒስትር ክሌበር ሶአሬስ አዲስ አበባ በተካሄደው 7ኛው ዓለም አቀፍ የአግሮ-ፉድ ኤክስፖ ላይ ለስፑትኒክ አፍሪካ ተናግረዋል።
ብራዚል በግብርናው ዘርፍ ያላትን የዳበረ ልምድ እና እውቀት ለደቡባዊው ዓለም ሀገራት ለማጋራት ዝግጁ እንደሆነችም ጠቁመዋል።
በብሪክስ ማዕቀፍ በሳይንስና በቴክኖሎጂ ላይ የተመሠረተ ጠንካራ የግብርና መድረክ በመፍጠር ፈተናዎችን መጋፈጥ አስፈላጊ እንደሆነም አፅዕኖት ሰጥተዋል።
የምግብና የግብርና ዘርፉን እንዴት ማሻሻል ይቻላል ለሚለው ጥያቄ ምላሽ ሲሰጡ "የብሪክስ እንቅስቃሴ ይህንን ፈተና ለመጋፈጥ የተሻለው እንቅስቃሴ ነው። ብራዚል ኢትዮጵያ ይህንን እንቅስቃሴ እንድትቀላቀል ስትጋብዝ ኢትዮጵያ ወሳኝ መሪ ሀገር እና በአፍሪካ እና አፍሪካ ሕብረት ዋነኛ የመሪነት ሚና ስለምትጫወት ነው። ይህንን ችግር ለመመከት በጋራ ለመሥራት አስበናን" ብለዋል።
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X