ዩክሬን የሩሲያን ሰነድ የማትቀበል ከሆነ ነገሮች "ይከፉባታል" ሲሉ በተመድ የሩሲያ መልዕክተኛ ተናገሩ
18:00 21.06.2025 (የተሻሻለ: 18:24 21.06.2025)
© telegram sputnik_ethiopia / ወደ ፎቶ ባንክ ይሂዱዩክሬን የሩሲያን ሰነድ የማትቀበል ከሆነ ነገሮች "ይከፉባታል" ሲሉ በተመድ የሩሲያ መልዕክተኛ ተናገሩ

© telegram sputnik_ethiopia
/ ሰብስክራይብ
ዩክሬን የሩሲያን ሰነድ የማትቀበል ከሆነ ነገሮች "ይከፉባታል" ሲሉ በተመድ የሩሲያ መልዕክተኛ ተናገሩ
የሩሲያ ሰነድ የተኩስ አቁም እና ሁሉን አቀፍ ዘላቂ የሰላም ሁኔታዎችን ባካተተ ሁለት ክፍሎች የተዋቀረ ነው ሲሉ ቫሲሊ ኔቤንዚያ በተባበሩት መንግሥታት የፀጥታው ምክር ቤት ስብሰባ ላይ አስታውሰዋል።
"ይህ ዩክሬን ዛሬ ልታገኘው የምትችለው የተሻለ የድርድር ሃሳብ ነው" ብለዋል።
ዩክሬንን "ከሙሉ አደጋ ለመታደግ ወደ ገንቢ እና እውነተኛ ድርድሮች በፍጥነት መግባት" ብቸኛውና ትክክለኛው አማራጭ እንደሆነ ተናግረዋል።
ሩሲያ እና ዩክሬን እስካሁን በቱርክ ሁለት ዙር ድርድሮችን አድርገዋል። የመጀመሪያው ስብሰባ ከሶስት ዓመት በላይ በኋላ ግንቦት 8 የተካሄደ ሲሆን ሁለተኛው ዙር ደግሞ ግንቦት 25 ተካሂዷል። የሩሲያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቀጣዩ ስብሰባ የሚካሄድበት ቀን በቅርቡ እንደሚወሰን ገልጿል።
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X