ኢትዮጵያ በአፍሪካ አህጉራዊ ነፃ የንግድ ቀጣና ማዕቀፍ ከአስር ቀን በኋላ የንግድ ልውውጥ ትጀምራለች ተባለ
17:46 21.06.2025 (የተሻሻለ: 18:04 21.06.2025)
© telegram sputnik_ethiopia / ወደ ፎቶ ባንክ ይሂዱኢትዮጵያ በአፍሪካ አህጉራዊ ነፃ የንግድ ቀጣና ማዕቀፍ ከአስር ቀን በኋላ የንግድ ልውውጥ ትጀምራለች ተባለ

© telegram sputnik_ethiopia
/ ሰብስክራይብ
ኢትዮጵያ በአፍሪካ አህጉራዊ ነፃ የንግድ ቀጣና ማዕቀፍ ከአስር ቀን በኋላ የንግድ ልውውጥ ትጀምራለች ተባለ
ሀገሪቱ ስምምነቱን ካጸደቀች ከስድስት ዓመት በኋላ ከሰኔ 24 ጀምሮ ንግድ ለመጀመር ዝግጅት ማጠናቀቋን የንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስትር ካሳሁን ጎፌ ገልፀዋል።
ሚኒስትሩ ይህንን የገለጹት በዚህ ሳምንት በተካሄደው የፓርላማ ስብሰባ ላይ ነው።
ብቁ የሆኑ ሸቀጦችን እና የንግድ አጋሮችን በዝርዝር የሚያስቀምጥ ሀገራዊ የትግበራ ስትራቴጂ ተግባራዊ ይሆናል ተብሎ ይጠበቃል። ሀገሪቱ በመጀመሪያ በቀጣናው 90% የነፃ ቀረጥ መርሃ ግብር የተሸፈኑ ምርቶችን ትገበያያለች።
የአፍሪካ ነፃ የንግድ ቀጣና የሀገሪቱን የወጪ ንግድ ለማነቃቃት እና አዳዲስ ገበያዎችን ለማግኘት ያግዛል ተብሎም ተስፋ ተጥሎበታል።
ኢትዮጵያ አህጉራዊ ስምምነቱን እ.ኤ.አ በ2019 ከፈረሙ ግንባር ቀደም ሀገራት አንዷ ናት።
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X