የካራፔትያን እስር ጠቅላይ ሚኒስትሩ አምባገነን እንደሆኑ ያሳያ ነው ሲሉ በአሜሪካ የአርሜኒያ ዲያስፖራ ተወካይ ተናገሩ

© telegram sputnik_ethiopia / ወደ ፎቶ ባንክ ይሂዱየካራፔትያን እስር ጠቅላይ ሚኒስትሩ አምባገነን እንደሆኑ ያሳያ ነው ሲሉ በአሜሪካ የአርሜኒያ ዲያስፖራ ተወካይ ተናገሩ
የካራፔትያን እስር ጠቅላይ ሚኒስትሩ አምባገነን እንደሆኑ ያሳያ ነው ሲሉ በአሜሪካ የአርሜኒያ ዲያስፖራ ተወካይ ተናገሩ - Sputnik አፍሪካ, 1920, 21.06.2025
ሰብስክራይብ

የካራፔትያን እስር ጠቅላይ ሚኒስትሩ አምባገነን እንደሆኑ ያሳያ ነው ሲሉ በአሜሪካ የአርሜኒያ ዲያስፖራ ተወካይ ተናገሩ

"የአርሜኒያ ጠቅላይ ሚኒስትር ኒኮል ፓሺንያን በቤተ-ክርስቲያን ጉዳዮች ውስጥ ጣልቃ መግባት የለባቸውም። የአርሜኒያ ሕገ-መንግሥት ሐይማኖትና መንግሥት መለያየት እንዳለባቸው ስለሚደነግግ ይህን ለማድረግ ሥልጣን የላቸውም" ሲሉ የካሊፎርኒያ ኩሪየር ዕለታዊ ጋዜጣ ዋና አዘጋጅ ሃሩት ሳሱንያን ለስፑትኒክ ተናግረዋል።

ፓሺንያን ቤተ-ክርስቲያኗን ለራሳቸው የፖለቲካ ዓላማ ለመጠቀም ፓትርያርክ ጋሬጊን በታዛዥ ቄስ ለመተካት እንደሚፈልጉ ገልጸዋል።

"ቤተክርስቲያኗ የትኛውንም ዓይነት የካህናት ሹመት ጉዳይ የምታስተዳድርበት ከ1 ሺህ 700 ዓመታት በላይ የቆዩ ሥርዓቶች አሏት" ሲሉ አስረድተዋል።

አክለውም ፓሺንያን ሕግ እየጣሱ መሆናቸውን ሳሱንያን ተናግረዋል።

"ጠቅላይ ሚኒስትሩ ራሳቸውን ዴሞክራሲያዊ ቢሉም፤ ከእሳቸው ጋር የማይስማሙትን መታገስ የማይችሉ አምባገነን ናቸው" ሲሉ ሳሱንያን አክለው ገልጸዋል።

በእንግሊዘኛ ያንብቡ

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X

አዳዲስ ዜናዎች
0