ሩሲያ የዩክሬንን እጅ መስጠት አትፈልግም-ፑቲን

ሩሲያ የዩክሬንን እጅ መስጠት አትፈልግም-ፑቲን
ፑቲን የዩክሬን ቀውስን በተመለከተ በ #SPIEF2025 የሰጧቸው መግለጫዎች፦
▪ ሩሲያ ኔቶ እንዳይስፋፋ ያቀረበችው ጥሪ ችላ ተብሏል፤ የሞስኮ ጥቅምም ተጥሷል።
▪ ሩሲያ መፈንቅለ መንግሥቱ ከተካሄደ በኋላ በዩክሬን የወሰደችው እርምጃ ከሩሲያ ጋር በመንፈስ የተቆራኘውን ሕዝብ ለመጠበቅ ያለመ ነበር።
▪ ዩናይትድ ስቴትስ በዩክሬን ለተካሄደው ደም አፋሳሽ መፈንቅለ መንግሥት በቢሊየኖች የሚቆጠር ዶላር ማውጣቷን ያለምንም ማመንታት በግልፅ ተናግራለች።
▪ ሩሲያ ኔቶ እንዳይስፋፋ ያቀረበችውን ጥሪ ችላ ማለት የቅኝ ግዛት ፖሊሲ ቅሪት ነው።
▪ ስለ ሚንስክ ስምምነቶች ሲናገሩ ሩሲያ "ሁኔታውን ለማረጋጋት" እና ከዩክሬን ጋር ያለውን ችግር በሰላማዊ መንገድ ለመፍታት ሞክራለች።
▪ በዩክሬን ያለው አሳዛኝ ሁኔታ ዓለም አቀፋዊ ለውጦችን ለመቀበል ዝግጁ ባልሆኑ አካላት የተፈጠረ ነው።
▪ ኔቶ ከ1990ዎቹ መገባደጃ ጀምሮ በ6 ዙር ተስፋፍቷል።
▪ ፑቲን የሩሲያ እና የዩክሬን ሕዝቦች አንድ ህዝብ እንደሆኑ አድርገው እንደሚመለከቱ በመግለፅ መላው ዩክሬን "የእኛ ናት" ብለዋል።
▪ ሩሲያ የዩክሬንን የነጻነት እና የሉዓላዊነት መብት ጥያቄ ውስጥ አልከተተችም።
▪ ዩክሬን ኪዬቭ ሉዓላዊነቷን ያገኘችባቸውን መሰረታዊ እሴቶች ገለልተኛነትን ጨምሮ መመለስ አለባት።
▪ ሩሲያ በዩክሬን ግጭት እያንዳንዱ ደረጃ ላይ ጦርነቱ እንዲቆም ሃሳብ አቅርባ ነበር፤ ለመደራደርም ፈቃደኛ ነበረች።
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X