በሳዑዲ አረቢያ ሁለተኛው ግዙፍ ወርቅ አውጪ በኢትዮጵያ ለመሠማራት ፍላጎት እንዳለው ገለፀ
15:49 20.06.2025 (የተሻሻለ: 16:04 20.06.2025)

© telegram sputnik_ethiopia
/ ሰብስክራይብ
በሳዑዲ አረቢያ ሁለተኛው ግዙፍ ወርቅ አውጪ በኢትዮጵያ ለመሠማራት ፍላጎት እንዳለው ገለፀ
የሳዑዲ ወርቅ አውጪ ድርጅት ልዑክ በኢትዮጵያ የማዕድን ዘርፍ ዙሪያ ከኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ኮሚሽን ኮሚሽነር ዘለቀ ተመስገን ጋር ተወያይቷል።
ኮሚሽነሩ ሀገሪቱ ተወዳዳሪ የኢንቨስትመንት ሥርዓት የመዘርጋት ሥራ እያከናወነች እንደሆነ አብራርተዋል፡፡
የሳዑዲ ወርቅ አውጪ ድርጅት በዓመት ሁለት ቶን ወርቅ ያመርታል። በሞሮኮ፣ ኡዝቤኪስታን እና በሌሎችም ሀገራት በወርቅ ምርት ላይ ተሠማርቷል።
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X