ኢትዮጵያ ባለፉት 11 ወራት ከውጪ ንግድ ከ7 ቢሊዮን ዶላር በላይ ገቢ አግኝታለች ተባለ
15:25 20.06.2025 (የተሻሻለ: 15:34 20.06.2025)

© telegram sputnik_ethiopia
/ ሰብስክራይብ
ኢትዮጵያ ባለፉት 11 ወራት ከውጪ ንግድ ከ7 ቢሊዮን ዶላር በላይ ገቢ አግኝታለች ተባለ
ገቢው በሀገሪቱ የወጪ ንግድ ታሪክ ከፍተኛው እንደሆነ የንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስትር ካሳሁን ጎፌ በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ቀርበው የእቅድ አፈጻጸም ሪፖርት ባቀረቡበት ውቅት ተናግረዋል።
በወጪ ንግድ ምቹ ምህዳር መፈጠሩ፣ የተለያዩ የሕግና አሠራር ማነቆዎች መፈታታቸው፣ ከላኪዎችና ከባለ ድርሻ አካላት ጋር በተሻለ ቅንጅት በመሠራቱ ለተመዘገበው ውጤት ትልቅ ድርሻ አለው ብለዋል።
የወጪ ንግድ ገቢው ከ2016 በጀት ዓመት ጋር ሲነጻጸር ከ 3 ነጥብ 96 ቢሊየን ዶላር በላይ ጭማሪ አሳይቷል።
ሊጠናቀቅ ሳምንታት በቀሩት በዚህ በጀት ዓመት መጨረሻ ከ 8 ቢሊየን ዶላር በላይ ገቢ ይገኛል ተብሎ እንደሚጠበቅም ጠቁመዋል።
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X