የሩሲያ-ኢትዮጵያ የሚኒስትሮች ስብሰባ በቀጣይ ዓመት ህዳር ወር ላይ ይካሄዳል ተባለ
14:13 20.06.2025 (የተሻሻለ: 14:34 20.06.2025)

© telegram sputnik_ethiopia
/ ሰብስክራይብ
የሩሲያ-ኢትዮጵያ የሚኒስትሮች ስብሰባ በቀጣይ ዓመት ህዳር ወር ላይ ይካሄዳል ተባለ
ይህ የተገለፀው የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ደኤታ አምባሳደር ሃዴራ አበራ እና በኢትዮጵያ የሩሲያ አምባሳደር ኢቭጌኒ ተርኪሂን በሁለቱ ሀገራት ግንኙነት ዙሪያ በተወያዩበት ወቅት ነው።
ሚኒስቴር ደኤታው ሩሲያ የኢትዮጵያ የረዥም ጊዜ አጋር መሆኗን ገልፀው፤ በኢኮኖሚ፣ በንግድ እና በኢንቨስትመንት ዘርፎች የሁለቱን ሀገራት ታሪካዊ ግንኙነት ማጠናከር አስፈላጊ መሆኑን አፅዕኖት ሰጥተዋል።
የሩሲያ ኩባንያዎች በኢትዮጵያ ያለውን ምቹ የኢንቨስትመንት ከባቢ ተጠቅመው መዋዕለ ነዋያቸውን ፈሰስ እንዲያደርጉ ጥሪ አቅርበዋል።
አምባሳደር ኢቭጌኒ ተርኪሂን በበኩላቸው ሩሲያ በኢኮኖሚ እና በማህበራዊ ዘርፎች የሁለትዮሽ ግንኙነቶችን የበለጠ ለማጠናከር ያላትን ዝግጁነት ማረጋገጣቸውን ከውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የተገኘው መረጃ ያሳያል።
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X