የደቡብ አፍሪካ ሕግ አውጪ ብሪክስ የአይኤምኤፍን የ "ድህነት" ሞዴል መተካት አለበት ሲሉ ተናገሩ
19:57 19.06.2025 (የተሻሻለ: 20:04 19.06.2025)
© telegram sputnik_ethiopia
/ ሰብስክራይብ
የደቡብ አፍሪካ ሕግ አውጪ ብሪክስ የአይኤምኤፍን የ "ድህነት" ሞዴል መተካት አለበት ሲሉ ተናገሩ
ከ #SPIEF2025 ጎን ለጎን ከስፑትኒክ አፍሪካ ጋር ቃለ መጠይቅ ያደረጉት የደቡብ አፍሪካ የጋውቴንግ ግዛት ፓርላማ አፈ-ጉባኤ ሞራካኔ ሞሱፕዮ አፍሪካ 1.4 ቢሊየን ሕዝብ ባቀፈው አህጉራዊ ነፃ የንግድ ቀጣና ያላትን ጠንካራ አቅም አጽንኦት ሰጥተዋል።
ደቡብ አፍሪካ ወደ አህጉሪቱ መግቢያ በር መሆን እንደምትችል በማንሳት፤ የሩሲያ የመሠረተ ልማት ኢንቨስትመንት ሁሉንም ተጠቃሚ እንደሚያደርግ ተናግረዋል።
ብሪክስ የራሱን የፋይናንስ ስርዓት ለመገንባት “አቅም” እና “በቂ ሀብት” እንዳለው ገልፀው፤ አሁን ላይ ያለውን ጥገኝነት ተችተዋል።
"በአይኤምኤፍ ላይ ያለው ጥገኝነት ድህነትን ብቻ ነው የሚፈጥረው፤ ድህነት ሥር እንዲሰድ ያደረገ ነው።" ብሪክስ መላውን የአፍሪካ ሀገራት የሚደግፍ ፖሊሲዎችን እንዲቀረፅ ጥሪ አቅርበዋል።
ስፑትኒክ አፍሪካ ለብሪክስ ያለውን ቅርበት በመጥቀስ፤ ሽፋኑን ወደ ጋውቴንግ እንዲያሰፋ ጋብዘዋል።
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X