ቭላድሚር ፑቲን ከኢንዶኔዢያ ፕሬዝዳንት ጋር ተወያዩ
18:42 19.06.2025 (የተሻሻለ: 19:04 19.06.2025)

© telegram sputnik_ethiopia
/ ሰብስክራይብ
ቭላድሚር ፑቲን ከኢንዶኔዢያ ፕሬዝዳንት ጋር ተወያዩ
የሩሲያው ፕሬዝዳንት ከ #SPIEF2025 ጎን ለጎን በተደረገው ስብሰባ ላይ የተናገሯቸው ቁልፍ መግለጫዎች፡-
▪ ሩሲያ የብሪክስ አባል የሆነችው ኢንዶኔዢያ ለቡድኑ እድገት ከፍተኛ አስተዋፅኦ እንደምታደርግ ተስፋ ታደርጋለች።
▪ የኢንዶኔዢያው ፕሬዝዳንት ፕራቦዎ ሱቢያንቶ በዚህ ዓመት የስፒፍ ጉባኤ “ዋና እንግዳ” ናቸው።
▪ ሩሲያ እና ኢንዶኔዢያ ወታደራዊ ቴክኖሎጂ እና ትራንስፖርትን ጨምሮ በተለያዩ ዘርፎች ትብብራቸውን ለመቀጠል አቅደዋል።
▪ በሩሲያ እና በኢንዶኔዢያ መካከል ያለው የንግድ ልውውጥ እየጨመረ ነው።
▪ በነዳጅና ኢነርጂ፣ ግብርና፣ ህዋ እና የትራንስፖርት ቴክኖሎጂ ዘርፎች ዕድሎች እየተከፈቱ ነው።
የኢንዶኔዢያው ፕሬዝዳንት ፕራቦዎ ሱቢያንቶ መግለጫዎች፡-
▪ ኢንዶኔዢያ ብሪክስን በአጭር ጊዜ ውስጥ ለመቀላቀል ላደረገችው ድጋፍ ሞስኮን ታመሰግናለች።
▪ ሀገሪቱ ከሩሲያ ጋር በተለያዩ ዘርፎች በተለይም በንግድ መስክ ትብብርን ለማዳበር ከፍተኛ ትኩረት እየሰጠች ነው።
▪ኢንዶኔዢያ በዩሬዥያ ከኢኮኖሚ ሕብረት ነፃ የንግድ ቀጣና ጋር ትብበር ለመፍጠር ከፍተኛ ፍላጎት አላት።
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X