"ብሪክስ ኢትዮጵያ ዶላር ላይ ያላትን ጥገኝነት በሂደት ይቀንሳል" ሲሉ የኢትዮጵያ ኢንደስትሪ ሚኒስቴር ኃላፊ ተናገሩ
18:33 19.06.2025 (የተሻሻለ: 18:54 19.06.2025)
© telegram sputnik_ethiopia / ወደ ፎቶ ባንክ ይሂዱ"ብሪክስ ኢትዮጵያ ዶላር ላይ ያላትን ጥገኝነት በሂደት ይቀንሳል" ሲሉ የኢትዮጵያ ኢንደስትሪ ሚኒስቴር ኃላፊ ተናገሩ

© telegram sputnik_ethiopia
/ ሰብስክራይብ
"ብሪክስ ኢትዮጵያ ዶላር ላይ ያላትን ጥገኝነት በሂደት ይቀንሳል" ሲሉ የኢትዮጵያ ኢንደስትሪ ሚኒስቴር ኃላፊ ተናገሩ
ኢትዮጵያ አግሮ-ኢንዱስትሪ ፓርኮችን በማልማት የገጠር ኢንዱስትሪ ልማትን ለማበረታታት እየሠራች እንደሆነ የሚገልፁት በኢንዱስትሪ ሚኒስቴር የተቀናጀ አግሮ-ኢንዱስትሪ ፕሮጀክት ድጋፍ አስተባባሪ አያልነህ አባዋ፤ ብሪክስ ኢንዱስትሪን ለማሳደግ በቂ ካፒታል ማግኘት የሚያስችል ተጨማሪ አቅም ይፈጥራል ብለው እንደሚያምኑ ለስፑትኒክ አፍሪካ ተናግረዋል።
"የብሪክስ አባል ሀገራት ውስጥ ተጨማሪ የገበያ አማራጭ አቅም አለ። ብሪክስ የራሱን የምንዛሪ ስርዓት ሲፈጥር በውጭ ምንዛሬ ላይ ያለንን ጥገኝነት ከጊዜ ወደ ጊዜ ይቀንሳል ብዬ አምናለሁ" ሲሉ አስተባባሪው አብራርተዋል።
አስተባባሪው ዛሬ በአዲስ አበባ በተከፈተው ሰባተኛው አግሮ ፉድ እና ፕላስት ፕሪንት ፓክ ኢትዮጵያ የንግድ ትርዒት በኢንደስትሪ በፓርኮቻ ውስጥ ካሉ ብዙ ባለሀብቶች ጋር ትስስር የመፍጠር አቅሙ የጎላ ነው ብለዋል።
አክለውም ኢትዮጵያ ከውጭ የሚገቡ ምርቶችን ለመተካት እየሠራች እንደሆነ አመልክተው፤ ሀገሪቱ ዓለም ሊገጥማት የሚችለውን የምግብ ቀውስ የመመከት አቅም እንዳላት ጥናቶች እንደሚያመላክቱ ገልፀዋል።
"በአፍሪካ፣ ኢትዮጵያ፣ ትልቅ እምቅ አቅም እንዳለ ይታወቃል። ወደፊት ኢትዮጵያ ዓለም አቀፍ የምግብ ገበያን እንደምትመራ ይታመናል። ከውጭ የሚገቡ ምርቶችን መተካት ብቻ ሳይሆን የዓለም አቀፍ የምግብ ገበያን ሰብረን መግባት እንችላለን" ሲሉ አስረድተዋል።
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X