ኢትዮጵያ እና ኬንያ የኤሌክትሪክ ኃይል ሽያጭ ስምምነታቸውን በድጋሚ መዋዋል እንደሚኖርባቸው ተገለፀ

© telegram sputnik_ethiopia / ወደ ፎቶ ባንክ ይሂዱኢትዮጵያ እና ኬንያ የኤሌክትሪክ ኃይል ሽያጭ ስምምነታቸውን በድጋሚ መዋዋል እንደሚኖርባቸው ተገለፀ
ኢትዮጵያ እና ኬንያ የኤሌክትሪክ ኃይል ሽያጭ ስምምነታቸውን በድጋሚ መዋዋል እንደሚኖርባቸው ተገለፀ - Sputnik አፍሪካ, 1920, 19.06.2025
ሰብስክራይብ

ኢትዮጵያ እና ኬንያ የኤሌክትሪክ ኃይል ሽያጭ ስምምነታቸውን በድጋሚ መዋዋል እንደሚኖርባቸው ተገለፀ

ኬንያ ከኢትዮጵያ የምታገኘውን የኤሌክትሪክ ኃይል በእጥፍ ለመጨመር በውጭ ጉዳይ በኩል ይፋዊ ጥያቄ አቅርባለች።

ከሶስት ዓመት በፊት ሁለቱ ሀገራት ባደረጉት የ25 ዓመት ስምምነት መሠረት ኢትዮጵያ በአሁኑ ወቅት ለኬንያ 200 ሜጋ ዋት የኤሌክትሪክ ኃይል ትልካለች። ከመጪው ዓመት ህዳር ወር ጀምሮ ደግሞ አቅርቦቱ ወደ 400 ሜጋ ዋት ከፍ እንደሚል ይጠበቅ ነበር።

ሆኖም ኬንያ የኢንዱስትሪ ኃይል ፍላጎቷ በመጨመሩ ምክንያት በስምምነቱ ከተቀመጠው ቀን በፊት ከኢትዮጵያ የምታስገባውን ኃይል ወደ 400 ሜጋ ዋት ለማሳደግ ፍላጎቷን ገልጻለች።

የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል የኮሚኒኬሽን ዳይሬክተር አቶ ሞገስ መኮንን የኬንያ ጥያቄ በስምምነቱ ላይ ያልተካተተ በመሆኑ ድጋሚ ድርድር እንደሚያስፈልግ ተናግረዋል።

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X

አዳዲስ ዜናዎች
0