ኢትዮጵያ የብሪክስ ባንክን ለመቀላቀል በምታደርገው ጥረት የተባበሩት አረብ ኤምሬቶችን ሙያዊ እገዛ ጠየቀች

© telegram sputnik_ethiopia / ወደ ፎቶ ባንክ ይሂዱኢትዮጵያ የብሪክስ ባንክን ለመቀላቀል በምታደርገው ጥረት የተባበሩት አረብ ኤምሬቶችን ሙያዊ እገዛ ጠየቀች
ኢትዮጵያ የብሪክስ ባንክን ለመቀላቀል በምታደርገው ጥረት የተባበሩት አረብ ኤምሬቶችን ሙያዊ እገዛ ጠየቀች - Sputnik አፍሪካ, 1920, 19.06.2025
ሰብስክራይብ

ኢትዮጵያ የብሪክስ ባንክን ለመቀላቀል በምታደርገው ጥረት የተባበሩት አረብ ኤምሬቶችን ሙያዊ እገዛ ጠየቀች

ጥያቄው የቀረበው በተባበሩት አረብ ኤምሬቶች የኢትዮጵያ አምባሳደር ዑመር ሁሴን ከሀገሪቱ የማዕከላዊ ባንክ ገዥ ካሊድ መሐመድ ጋር በተወያዩበት ወቅት ነው።

ኢትዮጵያ የብሪክስ ባንክ አባል ለመሆን ባቀረበችው ጥያቄ የተገኘው ድጋፍ እንዲፋጠን እና በሁለቱ ሀገራት መካከል ያለውን የባንክ ዘርፍ ግንኙነት የበለጠ ማጠናከር በሚቻልበት ዙሪያ ተወያይተዋል።

ኢትዮጵያ የፋናንስ ዘርፉን ክፍት ማድረጓ እና መንግሥት እየወሰዳቸው ያሉ እርምጃዎች አዲሱ የልማት ባንክ ካነገበው የመሠረተ-ልማት እና ቀጣይነት ያለው ልማት ዓላማ ጋር በቀጥታ የሚዛመድ መሆኑን ገልፀዋል፡፡

ኢትዮጵያ የባንኩ አባል ለመሆን በይፋ ጥያቄዋን አቅርባ ከአባል ሀገራቱ የፖለቲካ ድጋፍ እንዳገኘች በዩኤኢ የኢትዮጵያ ኤምባሲ አስታውሷል።

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X

አዳዲስ ዜናዎች
0