ፑቲን ከቻይና ፕሬዝዳንት ሺ ጂንፒንግ ጋር በስልክ ተነጋገሩ
13:46 19.06.2025 (የተሻሻለ: 14:04 19.06.2025)

© telegram sputnik_ethiopia
/ ሰብስክራይብ
ፑቲን ከቻይና ፕሬዝዳንት ሺ ጂንፒንግ ጋር በስልክ ተነጋገሩ
በመካከለኛው ምስራቅ ስላለው ሁኔታ መወያታቸውን የሩሲያው ፕሬዝዳንት ረዳት አስታውቀዋል።
በዩሪ ኡሻኮቭ የተሰጡ ሌሎች ቁልፍ መግለጫዎች፦
🟠 ሩሲያ እና ቻይና የተባበሩት መንግሥታት ቻርተርን የሚጥሱ የእስራኤል ድርጊቶችን በፅኑ አውግዘዋል።
🟠 በተጨማሪም ሞስኮ እና ቤጂንግ በመካከለኛው ምስራቅ ያለውን ሁኔታ በኃይል መፍታት እንደማይቻል ያምናሉ።
🟠 ፑቲን አስፈላጊ ከሆነ ሩሲያ የመካከለኛው ምስራቅ ግጭትን ለማሸማገል ዝግጁ መሆኗን አረጋግጠዋል።
🟠 የሩሲያ እና የቻይና መሪዎች በሚቀጥሉት ቀናት ከመካከለኛው ምስራቅ ጋር በተያያዘ ግንኙነቶችን እንዲያደርጉ እና መረጃ እንዲለዋወጡ ለሁለቱ ሀገራት አስተዳደሮች እና አገልግሎቶች ትዕዛዝ ለመስጠት ተስማምተዋል።
🟠 ፑቲን እና ሺ ጂንፒንግ የቡድን 7 የመሪዎች ስብሰባ ውጤቶችን ተወያይተዋል። በስብሰባው ተሳታፊዎች መካከል የነበሩትን አስቸጋሪ ጉዳዮችም ተነስተዋል።
🟠 ለዘለንስኪ የቡድን 7 የመሪዎች ስብሰባ በውጭ ሀገር ካደረጋቸው ጉዞዎች ሁሉ ስኬታማው እንዳልነበር ተነስቷል።
🟠 ፑቲን እና ሺ ጂንፒንግ ነሐሴ 27 በቻይና ተገናኝው ይወያያሉ።
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X