ለስድስተኛ ተከታተይ ቀናት የዘለቀው የኢራን- እስራኤል ግጭት የዛሬ ጠዋት መረጃዎች፦

© telegram sputnik_ethiopia / ወደ ፎቶ ባንክ ይሂዱለስድስተኛ ተከታተይ ቀናት የዘለቀው የኢራን- እስራኤል ግጭት የዛሬ ጠዋት መረጃዎች፦
ለስድስተኛ ተከታተይ ቀናት የዘለቀው የኢራን- እስራኤል ግጭት የዛሬ ጠዋት መረጃዎች፦ - Sputnik አፍሪካ, 1920, 19.06.2025
ሰብስክራይብ

ለስድስተኛ ተከታተይ ቀናት የዘለቀው የኢራን- እስራኤል ግጭት የዛሬ ጠዋት መረጃዎች፦

▪60 የእስራኤል ተዋጊ ጄቶች በቴህራን በአንድ ጥቃት የኢራን ፀረ-ታንክ ሚሳኤል ማምረቻ ቦታዎችን ጨምሮ ከ20 በላይ ኢላማዎችን እንደመቱ የእስራኤል መከላከያ ገልጿል፡፡

▪እስራኤል በሰሜን ምዕራብ ኢራን በአራክ የኒውክሌር ኮምፕሌክስ ውስጥ ያለውን የኒውክሌር ማብለያ አጥቅታለች። ተቋሙ አነስተኛ ጉዳት ብቻ እንደደረሰበትና ምንም ዓይነት የጨረር መፍሰስ እንዳልተከሰተ የኢራን መገናኛ ብዙኃን ዘግበዋል።

▪የእስራኤል አየር ኃይል ከቴህራን በስተምዕራብ በምትገኘው ካራጅ ከተማ ላይ የአየር ጥቃት እንደሠነዘረ የኢራን መገናኛ ብዙኃን ዘግበዋል።

▪ኢራን 2 ሺህ ኪሎ ሜትር ርቀት የሚምዘገዘገውን ሰጂል ሚሳኤል ለመጀመሪያ ጊዜ እስራኤል ላይ አስወንጭፋለች።

▪ኢንተርኔት ላይ የተለቀቁ ተንቀሳቃሽ ምስሎች ኢራን "በአዲስ ትውልድ ሚሳኤሎች" እስራኤልን እንዳጠቃች አሳይተዋል።

▪ሚዲያዎች እንደዘገቡት የኢራን ሚሳኤሎች ቴል አቪቭን መምታታቸውን ተከትሎ ሆሎን አካባቢን ጨምሮ ስድስት ፍንዳታዎች ተሰምተዋል።

▪እንደ ኢራን መገናኛ ብዙኃን ዘገባ ከሆነ ኢራን ጠዋት ላይ ያካሄደችው የባላስቲክ ሚሳኤል ጥቃት የእስራኤል ጦር የስለላ ካምፕ እና በቤር ሸቫ ከሶሮካ ሆስፒታል አጠገብ የሚገኘው ትልቅ የእስራኤል ጦር ዕዝ እና ኢንተለጀንስ (IDF C4I) ዋና መሥሪያ ቤት ላይ ያነጣጠረ ነበር።

▪የኢራን ሚሳኤሎች የእስራኤልን የአክሲዮን ገበያ መትተዋል።

▪የኢራን ታስኒም የዜና ወኪል የኢራን ሚሳኤሎች በሚደርሱበት ክልል ውስጥ የሚገኙ የአሜሪካ ወታደራዊ ተቋማትን ዝርዝር ይፋ አድርጓል።

▪የኢራን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ እስማኤል ባቃኢ አሜሪካ ጦርነቱን የምትቀላቀል ከሆነ "ቀጣናውን የለየለት ጦርነት" ውስጥ ትከታለች ሲሉ አስጠንቅቀዋል።

በእንግሊዘኛ ያንብቡ

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X

አዳዲስ ዜናዎች
0