የኮንጎ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ ግጭትን ለመፍታት ያስችላል የተባለው ረቂቅ ሰነድ ተዘጋጀ
11:39 19.06.2025 (የተሻሻለ: 11:54 19.06.2025)

© telegram sputnik_ethiopia
/ ሰብስክራይብ
የኮንጎ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ ግጭትን ለመፍታት ያስችላል የተባለው ረቂቅ ሰነድ ተዘጋጀ
ከሶስት ቀናት ውይይት በኋላ የተደረሠው ስምምነት ሰኔ 20 ይፈረማል ተብሎ ይጠበቃል።
በሰነዱ የተካተቱ ጉዳዮች፦
የግዛት አንድነት፣
ግጭት ማቆም እና ከተያዙ አካባቢዎች መልቀቅ፣
ትጥቅ ማስፈታት፣
የታጠቁ መንግሥታዊ ያልሆኑ አካላትን በሂደት ማዋኻድ፡፡
በተጨማሪም በአንጎላ ሽምግልና ከዚህ ቀደም በቀረበው ሃሳብ ላይ የተመሠረተ የጋራ የጸጥታ መዋቅርን ያካትታል።
የሩዋንዳ እና ኮንጎ ባለሙያዎች የሩዋንዳ ወታደሮች አካባቢውን ለቀው ስለሚወጡበት እና በሩዋንዳ ሁቱ አማፂ ቡድን፤ የሩዋንዳ ነፃ አውጪ ዲሞክራሲያዊ ኃይሎች፤ ላይ ስለሚደረገው የተቀናጅ እርምጃ በአንጎላ አሸማጋይነት ባለፈው ዓመት ሁለት ስምምነቶች ላይ ቢደርሱም፤ ስምምነቶቹ በሁለቱ ሀገራት ሚኒስቴሮች ሳይፀድቁ ቀርተዋል።
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X