የኢራን እና የእስራኤልን ግጭት በተመለከተ የዛሬ ምሽት መረጃዎች፦
21:36 18.06.2025 (የተሻሻለ: 23:04 18.06.2025)

© telegram sputnik_ethiopia
/ ሰብስክራይብ
የኢራን እና የእስራኤልን ግጭት በተመለከተ የዛሬ ምሽት መረጃዎች፦
🟠 ትራምፕ ቴህራን እጅ እንድትሰጥ በድጋሚ ጥሪ ያቀረቡ ሲሆን የኢራን እና እስራኤል ግጭት "ገና አላበቃም" በማለት አሜሪካ በኢራን የኒውክሌር ተቋማት ላይ ጥቃት ልትሰነዝር እንደምትችል ፍንጭ ሰጥተዋል።
🟠 በኩርዲስታን ግዛት እና በኢራን ከተሞች ሳቄዝ፣ አራክ እና ሬይ የእስራኤል የሞሳድ ወኪሎች መታሠራቸው ተዘግቧል።
🟠 የዓለም አቀፉ አቶሚክ ኢነርጂ ኤጀንሲ ዋና ዳይሬክተር ራፋኤል ግሮሲ ፎርዶ እስካሁን ጉዳት ባይደርስበትም፤ የእስራኤል ዘመቻ በናታንዝ እና ኢስፋሃን በሚገኙት የኢራን የኒውክሌር ማዕከላት ላይ ከፍተኛ ጉዳት አድርሷል ብለዋል።
🟠 የእስራኤል የሩቅ ቁጥጥር ስፓይክ ፀረ-ታንክ ሚሳኤሎች በኢራን አልቦርዝ ግዛት ውስጥ ተገኝተዋል።
🟠 በኢስፋሃን አቅራቢያ የኢራን የአየር መከላከያ ሠራዊት የጣለው የእስራኤል ሄርሜስ ሰው አልባ አውሮፕላን ፍርስራሽ ምሥል ይፋ ሆኗል።
🟠 የሩሲያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ ማሪያ ዛካሮቫ ስለ መካከለኛው ምስራቅ የኒውክሌር ግጭት መካካር በሰጡት አስተያየት “የእልቂት ጫፍ ላይ መደረሱን” እና በኢራን የኒውክሌር ተቋማት ላይ በየቀኑ ጥቃቶች አየተፈፀሙ እንደሆነ ተናግረዋል።
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X