የሩሲያ አልማዝ ማዕድን አውጪ ቡድን እና የአፍሪካ ሀገራት የአልማዝ ማዕድን አወጣጥ መስፈርት አዘጋጁ
18:32 18.06.2025 (የተሻሻለ: 18:54 18.06.2025)
© telegram sputnik_ethiopia / ወደ ፎቶ ባንክ ይሂዱየሩሲያ አልማዝ ማዕድን አውጪ ቡድን እና የአፍሪካ ሀገራት የአልማዝ ማዕድን አወጣጥ መስፈርት አዘጋጁ

© telegram sputnik_ethiopia
/ ሰብስክራይብ
የሩሲያ አልማዝ ማዕድን አውጪ ቡድን እና የአፍሪካ ሀገራት የአልማዝ ማዕድን አወጣጥ መስፈርት አዘጋጁ
እ.ኤ.አ በ2023 ሩሲያ በአፍሪካ አልማዝ አምራቾች ማህበር የታዛቢነት መቀመጫ እንዳገኘች የሩሲያው አልሮሳ የዓለም አቀፍ ትብብር ክፍል ኃላፊ ፒዮትር ካራክቺቭ ከ #SPIEF2025 ጎን ለጎን አስታውሰዋል።
የሩሲያ እና የአፍሪካ አልማዞች በአንድ ወጥ የምርት መስፈርት ላይ ተመስርተው ወደ ዓለም ገበያ መቅረባቸው አስፈላጊ ነውም ብለዋል።
እንደ ካራክቺቭ ገለጻ ነጠላ መስፈርቱ የሚከተሉትን ጉዳዮች ያካትታል፦
🟠የሠራተኛ መብቶች፣
🟠የኢንዱስትሪ ደህንነት፣
🟠የአካባቢ ጥበቃ፣
🟠ማህበራዊ ኃላፊነት።
ካራክቺቭ በሩሲያ እና በአፍሪካ አልማዝ አምራቾች ማህበር መካከል ያለውን ትብብር አስፈላጊነት አጽንዖት ሰጥተዋል። የአፍሪካ አጋሮች ጠንካራ አቋም ምዕራባውያን የሩሲያ አልማዝ ላይ ማዕቀብ ለመጣል ለሶስት ዓመታት ያደረጉትን ሙከራ እንዳገደውም ጠቁመዋል።
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X