አራት የኢትዮጵያ ቆዳ ፋብሪካዎች ዓለም አቀፍ የጥራት ደረጃ የእውቅና ሰርተፍኬት አገኙ
17:34 18.06.2025 (የተሻሻለ: 17:54 18.06.2025)

© telegram sputnik_ethiopia
/ ሰብስክራይብ
አራት የኢትዮጵያ ቆዳ ፋብሪካዎች ዓለም አቀፍ የጥራት ደረጃ የእውቅና ሰርተፍኬት አገኙ
ይህ የተገለፀው የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የኢንዱስትሪ ልማት ድርጅት በኢትዮጵያ ሲያካሂደው የቆየው "የቆዳ ልማት ዘላቂ ሥራ ፈጠራ ፕሮጀክት" ማጠቃለያ መርሐ ግብር ላይ ነው።
በዓለም አቀፉ የቆዳ የሥራ ቡድን እውቅና ያገኙ የቆዳ ፋብሪካዎች የትኞቹ ናቸው?
የወርቅ ደረጃ ሰርተፍኬት ያገኙ የቆዳ ፋብሪካዎች፦
ኤሊኮ አዋሽ
ኤሊኮ አቢሲኒያ
የብር ደረጃ ሰርተፍኬት
ባቱ ቆዳ ፋብሪካ
ኮልባ ታንሪ በቅርቡ የእውቅና ማረጋገጫ ኦዲቱን በማጠናቀቅ የአቻ ግምገማ በማድረግ ላይ ይገኛል፡፡
የአካባቢ ብክለትን በመቀነስ እንዲሁም የቆዳ ጥራት ደረጃን በማሻሻል ዓለም ዓቀፍ ተወዳዳሪ መሆናቸው የእውቅና ሰርተፍኬቱን እንዲያገኙ ትልቁን ድርሻ ይዟል ተብሏል፡፡
በኢትዮጵያ ዓለም አቀፍ የምስክር ወረቀት ያገኙ የቆዳ ፋብሪካዎች ቁጥር አሁን ላይ ስድስት መድረሱ የተገለፀ ሲሆን ይሄም ኢትዮጵያ በዓለም አቀፍ የቆዳ እሴት ሠንሠለት ውስጥ ያላትን ሚና ያጎላዋል መባሉን ኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት ዘግቧል።
በሰው ሰራሽ አስተውህሎት የበለፀገ ምሥል
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X