“ኢትዮጵያ ለቀጣናዊ ውህደትና የጋራ ብልፅግና ቁርጠኛ ናት”

© telegram sputnik_ethiopia / ወደ ፎቶ ባንክ ይሂዱ“ኢትዮጵያ ለቀጣናዊ ውህደትና የጋራ ብልፅግና ቁርጠኛ ናት”
“ኢትዮጵያ ለቀጣናዊ ውህደትና የጋራ ብልፅግና ቁርጠኛ ናት” - Sputnik አፍሪካ, 1920, 18.06.2025
ሰብስክራይብ

“ኢትዮጵያ ለቀጣናዊ ውህደትና የጋራ ብልፅግና ቁርጠኛ ናት”

የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ጌዲዮን ጢሞቴዎስ 4ኛው ዓመታዊ የናይል ወንዝ ፍትሐዊ ተጠቃሚነትና ቀጣናዊ ትስስር ኮንፍረንስ ላይ ባደረጉት ንግግር ኢትዮጵያ በክልሉ ተጨባጭ የኃይል ትስስር ለመፍጠር እየሠራች ነው ብለዋል፡፡

ለጅቡቲ፣ ለሱዳን እና ለኬንያ እየተላከ ያለውን የኤሌክትሪክ ኃይል በመጥቀስ፤ ግንኙነቱን ወደ ታንዛኒያ፣ ሶማሊያ እና ደቡብ ሱዳን ለማስፋፋት ዕቅድ እንዳለም አስታውቀዋል።

ሚኒስትሩ አክለውም በመቶ ሚሊዮኖች የሚቆጠሩ አፍሪካውያን በተለይም በምስራቅ አፍሪካ የኤሌትሪክ የኃይል እጥረት አለባቸው በማለት፤ ይህን ለመቅረፍ አስቸኳይና የተቀናጀ ክልላዊ እርምጃ ወሳኝ እንደሆነ ተናግረዋል።

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X

አዳዲስ ዜናዎች
0