ኢብራሂም ትራኦሬ ከ2025 የአፍሪካ ሕብረት መልዕክተኛ ጋር በሳህል ደህንነት እና ክልላዊ ተግዳሮቶች ዙሪያ ተወያዩ

ሰብስክራይብ

ኢብራሂም ትራኦሬ ከ2025 የአፍሪካ ሕብረት መልዕክተኛ ጋር በሳህል ደህንነት እና ክልላዊ ተግዳሮቶች ዙሪያ ተወያዩ

ኢብራሂም ትራኦሬ ከአፍሪካ ሕብረት ሊቀመንበር ልዩ መልዕክተኛ ቴቴ አንቶኒዮ ጋር ትናንት በቡርኪናፋሶ ርዕሰ መዲና ዋጋዱጉ ተገናኝተው ተወያይተዋል።

ከወቅቱ የአፍሪካ ሕብረት ሊቀመንበር የአንጎላ ፕሬዝዳንት ዣኦ ሎረንሶ መልዕክት ይዘው የመጡት ቴቴ አንቶኒዮ፤ የተልዕኳቸው አላማ በቡርኪና ፋሶ እና በሳህል ያለውን ሁኔታ ለመስማት መሆኑን ገልፀዋል።

  "መፍትሄ ለማግኘት እንደ አፍሪካውያን ምን የጋራ መንገዶችን መከተል እንደምንችል ለማወቅ ነው" ብለዋል።

አንቶኒዮ የአህጉራዊ ትብብርን አስፈላጊነት በማንሳት፤ ሕብረቱ የሳህል የጸጥታ ሁኔታ እየተባባሰ ሲሄድ ዝም ብሎ አይመለከትም ብለዋል።

በእንግሊዘኛ ያንብቡ

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X

አዳዲስ ዜናዎች
0