- Sputnik አፍሪካ, 1920
Sovereignty Sources
ዓለም በሉላዊነት ምክንያት ስትተሳሰር ፤ ፕሮግራሙም አፍሪካ ባላት እምቅ የተፈጥሮ ኃብት፣ በማደግ ላይ ባለው የሕዝብ ቁጥሯ ፣ በወጣት ኃይሏ እና በአህጉሪቱ ባሉ አዳዲስ ግኝቶችና የመፍትሄ ሃሳቦች ያላትን የመወዳደር አቅምና ጥቅም በሰፊው ይዳስሳል፡፡ እንኳን ወደ 'ሶቨርኒቲ ሶርስ' ፕሮግራም በደህና መጡ፣

ከፍታን የሚያልመው የአፍሪካ አቭዬሽን

ከፍታን የሚያልመው የአፍሪካ አቭዬሽን
ሰብስክራይብ
በአፍሪካ ሰማይ መልካም ዕድሎች ያንዣብባሉ! የአቪዬሽን ዘርፉ ለጠንካራ እድገት ተሰናድቷል፣ በዚህም ለአየር መንገዶች፣ ባለሃብቶች እና አገልግሎት ሰጪዎች አዲስ ዕድል ፈጥሯል። ነገር ግን ይህን ከፍታ የሚያነሳሳው ምንድነው - ደግሞስ ምን ወደኃላ ሊጎትተው ይችላል?
በዛሬው የሶቨርኒቲ ሶርስስ መሠናዶ በጥልቀት ለመወያየት የአቪዬሽን ዘርፍ ባለሙያው ዮናታን መንክር በእንግድነት ጋብዘናል።
የአቪዬሽን ዘርፉ ምን ያህል ሁነኛ መሣሪያ ስለመሆኑ ባለሙያው ዮናታን ሲያብራሩ፡-
“አቪዬሽን ወይም የአየር ትራንስፖርት የሚሰጠው ነገር የመንገደኞችን ሰዓት መቀነስ ነው። ይህ ዕውን የሚሆነው የአየር ትራንስፖርት ለንግድ  አገልግሎት  ተደርጎ ሲወሰድ ነው። ነገር ግን አቪየሽኑን በአጠቃላይ ከወሰድን፣ ብዙ ነገሮችን ማንሳት እንችላለን፣ የህክምና ቱሪዝም ፣ የግብርና አቪዬሽን ፣ በዋነኛነት  ለቱሪዝም ተግባራት ፣ ለአየር ካርታ ስራ እና ለምትለው ስራ ሁሉ አጠቃላይ የአቪዬሸን ዘርፉ ትልቅ ጥቅም ነው ያለው''
ብለዋል ። ዮናታን ዘርፉ በአህጉሪቱ እንዳይጎለብት ስለሚያደርጉት ማነቆዎች በተመለከተ ሲያስረዱ ፦
“የአፍሪካ አቪዬሽን ዘርፍ ዕድገት ማነቆ ከሆኑ ነገሮች መካከል መሠረ ልማት አንዱ ነው። መሰረተ ልማት ሲባል የረጅም ጊዜ ትስስር ነው። ይህ የአውሮፕላን ማረፊያ ወይም በዙሪያው የሚኖሩ ፋሲሊቲዎችን መገንባት ማለት አይደለም። ስለዚህ መንገዶች እጅግ አስፈላጊዎች ናቸው።ይህም ከአውሮፕላን ማረፊያ ተርሚናል የሚያልፍ መንገደኛ የሚጓዝበት ነው''
ሲሉ ተናግረዋል በአፍሪካ በዘርፉ ያሉ ትብብሮችም ፣ ከኢትዮጵያ ጠቃሚ ልምዶች የሚቀሰምባቸው ቢሆኑ አዋጭ ስለመሆኑ የአቪዬሽን ባለሙያው ዮናታን መንክር ተናግረዋል።
“አንዳንድ የአፍሪካ ሀገራት የጎለበተ የሠው ኃይልና ቴክኖሎጂ እንዲኖራቸው በአፍሪካ ቀዳሚ ወደሆነው  የኢትዮጵያ አየር መንገድ መጠጋታቸው ጥሩ ማሳያ ነው። ነገር ግን ይህ የጥቂቶች ብቻ ሳይሆን የብዙዎች ነው መሆን ያለበት። ስለዚህ ሀገራት በቴክኖሎጂ፣ በምጣኔ ሐብትና በሰው ኃይል አጋርነት ላይ እንዲተባበሩ ፍላጎት ሊኖር ይገባል።  እነዚህ ነገሮች ለአቪዬሽን ኢንዱስትሪ እድገት እና ልማት በጣም ቁልፍ ናቸው” ብለዋል።
ስለ አቪዬሽን ዘርፉ የበለጠ ለመረዳት በስፑትኒክ አፍሪካ ተሰናድቶ የሚቀርበውን ይህን በእንግሊዝኛ ቋንቋ የተሰናዳውን የሶቨርኒቲ ሶርስስ መሠናዶ ይከታተሉ ።
ለማድመጥ ዝግጁ ነዎት?
አዳዲስ ዜናዎች
0