ናይሮቢ ውስጥ የጦማሪው አልበርት ኦጅዋንግን ሞት ተከትሎ ተቃውሞ ተቀሰቀሰ
17:01 17.06.2025 (የተሻሻለ: 17:24 17.06.2025)
© telegram sputnik_ethiopia
/ ሰብስክራይብ
ናይሮቢ ውስጥ የጦማሪው አልበርት ኦጅዋንግን ሞት ተከትሎ ተቃውሞ ተቀሰቀሰ
🪧 የ31 ዓመቱ መምህርና ጦማሪ በፖሊስ ቁጥጥር ስር እያለ መሞቱን ተከትሎ በዛሬው ዕለት በናይሮቢ ማዕከላዊ የንግድ አካባቢዎች ተቃውሞዎች ተቀስቅሰዋል።
ተቃዋሚዎች የፖሊስ ምክትል ኢንስፔክተር ጄኔራል ኤሊዩድ ላጋት ለኦጅዋንግ ሞት ምክንያት ናቸው በማለት እንዲታሰሩና ለፍርድ እንዲቀርቡ ጠይቀዋል፡፡ ላጋት ከሥልጣናቸው ቢነሱም ብዙዎች ይህ እርምጃ በቂ አይደለም እያሉ ነው።
የቅድሚያ የፖሊስ ሪፖርቶች ኦጅዋንግ በእስር ቤት ውስጥ ጭንቅላቱ ከግድግዳ ጋር ከተጋጨ በሗላ እንደወደቀ ቢገልጹም፤ የመንግሥት የአስከሬን ምርመራ የኃይል ምት፣ የአንገት መታነቅና በርካታ ጉዳቶች እንደደረሱበት አሳይቷል።
በማህበራዊ ሚዲያ ላይ እየተሰራጩ ያሉ ምሥሎች ያልታወቁ ግለሰቦች ሰልፉን ለማደናቀፍ ሲሞክሩ ያሳያል።
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X