ኢትዮ ቴሌኮም እና የኦሮሚያ የግብርና ቢሮ የ "ስማርት ግብርና" አገልግሎት ለማቅረብ ተስማሙ

© telegram sputnik_ethiopia / ወደ ፎቶ ባንክ ይሂዱኢትዮ ቴሌኮም እና የኦሮሚያ የግብርና ቢሮ የ "ስማርት ግብርና" አገልግሎት ለማቅረብ ተስማሙ
ኢትዮ ቴሌኮም እና የኦሮሚያ የግብርና ቢሮ የ ስማርት ግብርና አገልግሎት ለማቅረብ ተስማሙ - Sputnik አፍሪካ, 1920, 17.06.2025
ሰብስክራይብ

ኢትዮ ቴሌኮም እና የኦሮሚያ የግብርና ቢሮ የ "ስማርት ግብርና" አገልግሎት ለማቅረብ ተስማሙ

መግባቢያው በግብርናው ዘርፍ ምርታማነትን፣ ቅልጥፍናን፣ ጥራትን፣ ትርፋማነትንና የገበያ ትስስርን በማሳደግ የዘርፉን የእሴት ሰንሰለት በዘላቂነት ለማዘመን ጉልህ ሚና እንደሚኖረው ተገልጿል።

ይህ ሁለገብ የ "ዳታ ሶሉሺን" የኢትዮ ቴሌኮምን የዲጂታል ኔትወርክ መሠረተ ልማት በመጠቀም መረጃዎችን ወደ ዳታ ማዕከሉ ለትንተና ይልካል ተብሏል።

አርሶ አደሩ ወቅታዊ የገበያ ዋጋን ጨምሮ ሌሎች በርካታ መረጃዎችን የሚያገኝበት ነው የተባለለት አገልግሎቱ፤ ከግብዓት አቅራቢዎችና ከአርሶ አደሮች ጀምሮ በግብርናው ሂደት ውስጥ ያሉ የተለያዩ ተዋናዮችን በዲጂታል በማገናኘት ለመረጃ ትንተና ያገለግላል ሲል ኢትዮ ቴሌኮም አስታውቋል።

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X

አዳዲስ ዜናዎች
0