ኮትዲቯር በትንሹ 100 ቶን የሚመዘን የወርቅ ክምችት አገኘች
14:36 17.06.2025 (የተሻሻለ: 14:54 17.06.2025)

© telegram sputnik_ethiopia
/ ሰብስክራይብ
ኮትዲቯር በትንሹ 100 ቶን የሚመዘን የወርቅ ክምችት አገኘች
ዓለም አቀፍ ደረጃውን የጠበቀው የወርቅ ክምችት የተገኘው በቡንካኒ ክልል ዶሮፖ ተብሎ በሚጠራው አካባቢ ነው።
ሬዞሉት የማዕድን ኩባንያ በትናትናው ዕለት ጠቅላይ ሚኒስትር ሮበርት ቤውግሬ ማምቤ በተገኙበት ግኝቱን ይፋ አድርጓል።
ኩባንያው የማዕድን ማውጫ ግንባታ ላይ 510 ሚሊዮን ዶላር ኢንቨስት ለማድረግ አቅዷል።
ኩባንያው ተጨማሪ 204 ሚሊዮን ዶላር በሀገሪቱ ውስጥ ለሚያደርገው የማዕድን ፍለጋ ኢንቨስት ይደረጋል።
የማዕድን ማውጫው ግንባታ እ.ኤ.አ በ2026 የመጀመሪያው ሩብ ዓመት ይጀምራል።
የማዕድን ማውጫው እ.ኤ.አ በ2028 ሥራ የሚጀምር እና ከ20 ዓመታት በላይ የሚሠራ ሲሆን ከ3 ሺህ በላይ የሥራ ዕድሎችን ይፈጥራል።
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X