ኢትዮጵያ 10 ቢሊየን ዶላር ይፈጃል የተባለ ፈጣን መንገድ ለመገንባት እቅድ እንዳላት ተገለፀ
14:26 17.06.2025 (የተሻሻለ: 14:34 17.06.2025)
© telegram sputnik_ethiopia / ወደ ፎቶ ባንክ ይሂዱኢትዮጵያ 10 ቢሊየን ዶላር ይፈጃል የተባለ ፈጣን መንገድ ለመገንባት እቅድ እንዳላት ተገለፀ

© telegram sputnik_ethiopia
/ ሰብስክራይብ
ኢትዮጵያ 10 ቢሊየን ዶላር ይፈጃል የተባለ ፈጣን መንገድ ለመገንባት እቅድ እንዳላት ተገለፀ
የኢትዮጵያ መንግሥት 2 ሺህ ኪሎ ሜትር የሚያካልል የፈጣን መንገድ መሠረተ ልማት ለመገንባት ማቀዱን ኢንቨስትመንት ኮሚሽን ከገንዘብ ሚኒስቴር ጋር በመተባበር ባሳተመው አዲስ የኢንቨስትመንት “ስምምነት መጽሐፍ” ውስጥ ተገልጿል።
በውጥኑ የተካተቱ የመንገድ መስመሮች፦
🟠 አዲስ አበባ–ኮምቦልቻ–ደሴ፦ 352.2 ኪ.ሜ (2.32 ቢሊየን ዶላር)፣
🟠 አዲስ አበባ–ጂማ፦ 345.5 ኪ.ሜ (2.03 ቢሊየን ዶላር)፣
🟠 አዲስ አበባ–ደብረ ማርቆስ፦ 317.6 ኪ.ሜ (1.64 ቢሊየን ዶላር)።
ፕሮጀክቱን በመንግሥትና በግሉ ዘርፍ ትብብር እንዲሁም በዓለም አቀፍ ተጫራቾች ለመተግበር መታቅዱን የሀገር ውስጥ ሚዲያ ዘግቧል፡፡
በሰው ሰራሽ አስተውህሎት የበለፀገ ምሥል
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X