አልጄሪያ በ2026 በዱረም ስንዴ ምርት ራሷን እንደምትችል አስታወቀች
16:38 16.06.2025 (የተሻሻለ: 16:54 16.06.2025)

© telegram sputnik_ethiopia
/ ሰብስክራይብ
አልጄሪያ በ2026 በዱረም ስንዴ ምርት ራሷን እንደምትችል አስታወቀች
የሀገሪቱ የግብርና ሚኒስትር ዩሴፍ ቾርፋ ይህ ክብረ ወሰን የሆነ የምርት እድገት የተመዘገበዉ በተሻሻለ የግብርና ስትራቴጂ ምክንያት መሆኑን ገልፀዋል።
እ.ኤ.አ በ2024/2025 የሚመረተው ሰብል በደቡባዊ ክልሎች በአንድ ሄክታር እስከ 80 ኩንታል የሚደርስ ምርት እንደሚያስገኝና በሰሜናዊ የሀገሪቱ ክፍል ደግሞ ከፍተኛ መሻሻል እንደሚታይ አስታውቀዋል።
ስኬቱን ያመጡ ምክንያቶች፦
🟠የተሻሻለ የመሬት አጠቃቀም እና አርሶ አደሮች ትምህርት፣
🟠ለአካባቢው የአየር ንብረት ተስማሚ የሆኑ የስንዴ ዝርያዎችን በማስተዋወቅ፣
🟠ዘመናዊ የግብርና መሠረተ ልማት።
የሚጠበቁ ውጤቶች፦
🟠በገቢ ምርት ላይ ጥገኝነትን መቀነስ፣
🟠የውጭ ምንዛሪ ክምችትን መጠበቅ፣
🟠የሀገሪቱን የምግብ ሉዓላዊነት ማጠናከር።
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X