ፕሬዝዳንት ትራኦሬ ለሀገሪቱ ዘላቂ ልማት ቁልፍ የሰው ኃይል ስልጠና እና በሀገር ምርቶችን ማቀነባበር ወሳኝ መሆናቸውን ገለፁ

ፕሬዝዳንት ትራኦሬ ለሀገሪቱ ዘላቂ ልማት ቁልፍ የሰው ኃይል ስልጠና እና በሀገር ምርቶችን ማቀነባበር ወሳኝ መሆናቸውን ገለፁ
የቡርኪና ፋሶው መሪ ትናንት ማንጋን በጎበኙበት ወቅት በራስ የመተማመን እና የጀግነኝነትን አስፈላጊነት አፅንዖት ሰጥተዋል።
የፕሬዝዳንቱ ስትራቴጂ በአምስት ዋና ዋና ዘርፎች ላይ ያተኩራል፦
⏺ የሀገር ውስጥ ማቀነባበሪያዎች፦ ትራኦሬ በርካሽ ዋጋ ወደ ውጭ ሀገራት የሚላከውን የጥሬ ጥጥ ምርት በመተቸት ያስቆሙ ሲሆን ምርቱን በማቀነባበር ለሆስፒታል እና ለተለያዩ አገልግሎቶች የሚጠቅሙ ግብአቶችን ለማመምረት አቅደዋል።
⏺ የሙያ ስልጠና፦ ላቦራቶሪዎች እና የቴክኒክ ክፍሎችን በማቋቋም ቴክኒሻኖችን፣ ሴቶችን እና ወጣቶችን የግብርና መሳሪያዎችን በማምረት እና በኢንዱስትሪ ክህሎቶች ለማሰልጠን አቅደዋል።
⏺ የክልል ኢንዱስትሪ፦ ወጪዎችን ለመቀነስ እና የአካባቢውን ኢኮኖሚ ለማሳደግ እያንዳንዱ ክልል የራሱ የሆነ የኢንዱስትሪ ዞን ይኖረዋል፤ በዚህም ክልሎቹ የየራሳቸውን የተለያዩ ሀብቶች ይጠቀማሉ።
⏺ የእንቅስቃሴ ገደቦችን ማሻሻል፦ እ.ኤ.አ በ2026፣ "ፋሶ ሜቦ" ተብሎ በተሰየመው እንቅስቃሴ እያንዳንዱ ክልል የአካባቢውን ሠራተኞች በመቅጠር የራሱ የሆነ የመንገድ ግንባታ ቡድን እንዲኖረው ይደረጋል።
⏺ የውሃ አቅርቦት፦ መንግሥት ግድቦችን ይገነባል፣ ከአንድ ሺህ ሜትር በላይ ጥልቀት ያለው ቁፋሮ ያካሂዳል በተጨማሪም ግብርናን ለመደገፍ የውሃ ማጠራቀሚያዎችን ያድሳል።
ትራኦሬ የቡርኪና ፋሶ የወደፊት ዕጣ ፈንታ በራስ መተማመን እና ከቅኝ ግዛት አሠራሮች ነፃ በመውጣት ላይ እንደሚገነባ ያምናሉ።
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X